“ዴቪድ ሲልቫ ለማንችስተር ደርቢ ይሰለፋል”- ፔፕ ጓርዲዮላ

Image result for SILVA

ከማንችስተር ደርቢው ጨዋታ ውጭ መሆኑ ሲነገርለነት የነበረው ስፔናዊው ኮከብ ዴቪድ ሲልቫ የፊታችን እሁድ በሚደረገው ጨዋታ ላይ ከጉዳቱ አገግሞ እንደሚደርስ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ አረጋግጠዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ማንችስተር ሲቲ ዌስትሀምን 2-1 ሲረታ የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆጠር ክለቡን ከአቻ ውጤት የታገደው ኮከብ ጥሩ ስሜት እየተሰማው እንዳልሆነ በመግለጽ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ዩክሬን እንዳላቀና መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ግን የመሀል ሜዳ ጥበበኛው በወሳኙ ፍልሚያ ላይ እንደሚሰለፍ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

እርሱ በጨዋታው ይሰለፋል፡፡ ዶክተሮቹ እርሱ በሳንቱ መጀመሪያ  በጨዋታው የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ነው ብለው የነበረ ቢሆንም ከእነርሱ ጋር በመነጋገር እንዲሰለፍ ወስነናል ይህም ለኛ ጥሩ ውሳኔ ነው ፡፡ በማለት የዴቪድ ሲልቫ መመለስ እንደሚጠቅማቸው አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ሊጉን ከተከታዩ ማችስተር ዩናይትድ በ8 ነጥቦች በመብለጥ በ43 ነጥቦች እየመራ የሚገኝ ሲሆን በ15 ሳምንታትም 46 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

Advertisements