ጁቬንቱስ ከ ኢንተር | የጣሊያን ሴሪ አ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

ጁቬንቱስ የኢንተር ሚላን በሴሪ አው ያለመሸነፍ ጉዞን ቅዳሜ ምሽት የመግታት ውጥን ይዞ ወደሜዳ ይገባል።

የማሲሚላኖ አሌግሪው ቡድን በደረጃው የሰንጠረዝ አናት ላይ የሚገኘውን ኢንተር ሚላንን በሶስት ነጥቦች በመከተል ሰባተኛ ተከታታይ የሴሪ ኣ ዋንጫ ድሉን የማሳካትም ዕቅድ አለው።

ጁቬንቱስ ባለፈው ሳምንት የናፖሊን ያለመሸነፍ ጉዞ በመግታት የሉቺያኖ ስፓሌቲውን ቡድን በጣሊያኑ ሊግ ያልተሸነፍ ብቸኛው ክለብም አድርጎታል።

ኢትዮአዲስ ስፖርትም ስለዚህ የሳምንቱ የጣሊያን ታላቅ ጨዋታ ሊያውቋቸው ይገባሉ ያለቻቸውን መሰረታዊ ነጥቦች እንደሚከተለው አሰናድታለች። 

ጨዋታው መቼ እና የት ይደረጋል?

ይህ አጓጊ ጨዋታ ቅድሜ ህዳር 30፣ 2010 ዓ.ም ከምሽት 3፡45 አንስቶ በጁቬንቱስ ስታዲየም ላይ የሚደረግ ነው።

የሁለቱ ቡድኖች የእርስ በእርስ ግንኙነት

ግምታዊ አሰላለፎች 

ጁቬንቱስ፦ 4-2-3-1

ኢንተር፦ 4-2-3-1

ቁጥራዊ እውነታዎች

  • የቅርብ ጊዜ ውጤቶች የሚያሳዩት ጁቬንቱስ የማሸነፍ ብልጫ እንዳለው ነው። አዛውንቷ ከኢንተር ሚላን ጋር በሜዳዋ ካደረገቻቸው ያለፉት የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች አራቱን ድል ማድረግ ችላለች። 
  • ሁለቱ ክለቦች ባደረጓቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች አንዱ ብቻ አቻ ውጤት ተመዝግቦበታል።
  • የማሲሚላኖ አሌግሪው ቡድን ባለፈው ማክሰኞ ኦሎምፒያኮስን በሻምፒዮንስ ሊግ ማሸነፍ የቻለበት የ2ለ0 ድል በተከታታይ ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች መረቡን ያላስደፈረበት ጨዋታ ነው። ከዚህ መካከል ዳግሞ ከባርሴሎና ጋር እና ከናፖሊ ጋር ያደረጋቸው ጭዋታዎች ይገኙበታል።
  • የሉቺያኖ ስፓሌቲው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን በሴሪ ኣው ላይ ሽንፈት ያልገጠመው ብቸኛ ክለብ ነው።  እስከሁንም 12 ጨዋታ አሸንፎ ሶስት ጨዋታዎችን ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቆ 39 ነጥቦችን መሰብሰብ ችሏል።
  • ኢንተር ከአታላንታ፣ ካግሊያሪ፣ እና ሼቮ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ባደረግቸው ሶስት ጨዋታዎች 10 ግቦችን በማስቆጠር ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።
  • ኢንተሮች በዚህ የውድድር ዘመን 16 ግቦችን ያስቆጠረላቸው አርጄንቲናዊ አጥቂ ማሪዮ ኢከርዲ በዚህ ጨዋታ ላይ የሚሰለፍ መሆኑ በራስ መተማመናቸውን ከፍ ያደርግላቸዋል። ክሮሺያዊው የክንፍ ተጫዋችም ኢቫን ፔርሲችም በስሙ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ ስድስት የግብ ዕድሎችን ደግሞ ማመቻቸት ችሏል።
Advertisements