ማንችስተር ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ | የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን በ15 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አልገጠመውም። 

ይህ የውጤት ጉዞው ደግሞ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በስምንት እንዲያሳድግ አስችሎታል። ይህን ጨዋታ በማሸነፍም የነጥብ ልዩነቱን ከዚህም በላይ የማድረግ ውጥን ይዞ የሚጫወትም ይሆናል።

የሆዜ ሞሪንሆው ቡድን በሜዳው ሽንፈት የሚደርስበት ከሆነ ግን ያለውን የነጥብ ልዩነት መልሶ ለማጥበብ በሚደረገ ፍልሚያ የቀድሞ ሞሮላቸውን ይዘው ለመገኘት በእጅጉ ይቸግራቸዋል።

ጨዋታ

ማን ዩናይትድ ከ ማን ሲቲ

ቀን

እሁድ ታህሳስ 1፣ 2010ዓ.ም

ሰዓት

ምሽት 1፡30


የቲቪ ስርጭት

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ ከታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ሱፐር ስፖርት 3፣ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ደግሞ ቢኢንስፖርት 2 እና 11 ላይ ጨዋታውን በአረብኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ ኮሜንታተሮች፣ እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም ተመልካቾች ይህን ጨዋታ በስካይ ስፖርትስ ፕሪሚየር ሊግ የቲቪ ቻነል መመልከት የሚችሉ ሲሆን፣ በኢንትርኔት ላይቭ ስትሪሚንግ ደግሞ በስካይ ጎ መመልከት ሲችሉ፣ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ በፉቦ ቲቪ ጨዋታውን ባላይቭ ስትሪሚንግ መመልከት ይችላሉ። 

የቡድን ስብስብ

የመጫወቻ ቦታ

የማን ዩናይትድ ተጫዋቾች

ግብጠባቂዎች

ሮሜሮ፣ ደ ኽያ፣ ፔሬራ

ተከላካዮች

ሊንዴሎፍ፣ ጆንስ፣ ሮኾ፣ ስሞሊንግ፣ ብሊንድ፣ ሻው፣ ቫሌንሺያ፣ ቱአንዜቤ፣ ዳርሜን 

አማካኞች

ማታ፣ ሊንጋርድ፣ ያንግ፣ ሄሬራ፣ ሚክሂታሪያን፣ ማቲች፣ ፌላይኒ፣ ሚቼል፣ ማክ ቲሞናይ

አጥቂዎች

ሉካኩ፣ ኢብራሂሞቪች፣ ማርሺያል፣ ራሽፎርድ

የቡድን ዜናዎች

ማንችስተር ዩናይትድ የሶስት ጨዋታዎች ቅጣት የተጠለበትን ፖል ፖግባን እንዲሁም በጉዳት ላይ የሚገኙትን ሚካኤል ካሪክን እና ኤሪ ቤሊን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተጫዋቾቾቹን ሳያሰልፍ ይህን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

ሞሪንሆ ኒማኒያ ማቲች ቀላል የጉጭት ጉዳት እንደገጠመው ነገር ግን በዚህ ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል  እንዲሁም ማሩዋን ፌላኒ ዘግይቶ በሚደረግለት የህክምና ምርመራ የመሰለፍ አለመሰለፉ ጉዳይ እንደሚወሰን አርብ ዕለት ተናግረዋል። ከዚህ ውጪ ግን ዝላታን ኢብራሂሞቪችና ፊል ጆንስ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ናቸው።

የዩናይትድ ግምታዊ የመጀመሪያ አሰለለፍ: ደ ኽያ፣ ሊንዴሎፍ፣ ሮኾ፣ ስሞሊንግ፣ ያንግ፣ ቫሌንሺያ፣ ማቲች፣ ሊንጋርድ፣ ሄሬራ፣ ማርሺያል፣ ሉካኩ 

የመጫወቻ ቦታ

የማን ሲቲ ተጫዋቾች

ግብጠባቂዎች

ኤደርሰን፣ ብራቮ፣ ግሪምሻው

ተከላካዮች

ዎከር፣ ዳኒሎ፣ ኮምፓኒ፣ ስቶንስ፣ ማንጋላ፣ ኦታሜንዲ፣ አዳራቢዮ፣ ዱሃኔይ

አማካኞች

ስተርሊንግ፣ ጉንዶጋን፣ ዳ.ሲልቫ፣ ደ ብሩይኔ፣ ደልፍ፣ በ. ሲልቫ፣ ሳኔ፣ ፈርናንዲንሆ፣ ቱሬ፣ ዚንቼንኮ፣ ዲያዝ፣ ፎደን 

አጥቂዎች

አጉዌሮ፣ ኼሱስ፣ ንሜቻ

የቡድን ዜናዎች

የዴቪድ ሲልቫ ወቅታዊ ጤንነት የጋርዲዮላ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ቢቆይም ካታላኖዊያዊው ግን አርብ ዕለት አማካኙ ለመጫወት ዝግጁ መሆኑን ገልፅዋል።

ምንም እንኳ የሁለቱ ተጫዋቾች የብቃት ሁኔታ መሻሻል አለመሻሻሉ ከጨዋታው በፊት የሚታይ ቢሆንም የቪንሰንት ኮምፓኒ እና ፋቢያን ደልፍ ወቅታዊ አካላዊ ብቃት ግን አሳሳቢ ነው። ሙሉ ለሙሉ በዚህ ጨዋታ ላይ አለመሰለፉ እርግጥ የሆነው የሲቲ ተጫዋች ግን ቤንጃሚን ሜንዲይ ብቻ ነው።

የሲቲ የመጀመሪያ ግምታዊ አሰላለፍ: ኤደርሰን፣ ኦታሜንዲ፣ ስቶንስ፣ ኮምፓኒ፣ ዎከር፣ ዳኒሎ፣ ደ ብሩይኔ፣ ደልፍ፣ ስተርሊንግ፣  ዴ.ሲልቫ፣ አጉዌሮ

አሰልጣኞቹ ስለጨዋታው የተናገሩት

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ፡ ስለማንችስተር ከተማ ህዝቦች የተለዩ መሆን የተናገሩት

“እውነቱን ለመናገር እኛ በስተመጨረሻ የምንፈልው ሶስት ነጥቦችን ነው። በዚህ ከተማ ውስጥ የተወለዱ ሰዎች እና የቀለም ስሜታቸው ጥሩ የሆነ አዎንታዊ ባላንጣነት አለው። ጨዋታውም ልዩ ነው ብዬ አስባለሁ።

“ለእኔም በከተማው ከሚገኝ ምርጥ ቡድን አንዱን መግጠሜ ጨዋታውን ትልቅ ጨዋታ ያደርገዋል። ካለፈው ዓመት የተሻለ አሁን ጥሩ ቡድን ነን። ሲቲም ካለፈው የውድድር ዘመን በተሻለ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ።”

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ: “ወደኦትራፎርድ የመሄድ መሆኔ ያኮራኛል። እዚህ የተገኘነውም ለዚህ ነው። ያለጥርጥርም ደስተኛ እሆንበታለሁ። 

“እዚያ ደርሼ ለመጫወትም መጪውን ጊዜ እየተመለከትኩ ነው። እነሱን ማሸነፍ የሚያስችለንን ስራ ሁሉ ለመስራትም ሆነ በዚያ መገኜቴንም እወደዋለሁ።” 

የጨዋታው እውነታዎች

የሁለቱ ክለቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት

 • ዩናይትድ ባለፉት 12 የፕሪሚየር ሊጉ የማንችስተር ደርቢ ጨዋታዎች (ካለፉት 45 ግንኙነታቸው) በሰባቱ ሽንፈት ደርሶበታል።
 • ሁለቱ ክለቦች የደረጃ ስንጠረዡ አናት ላይ በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ በተከታታይ በመቀመጥ የደርቢ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ከ2013 ወዲህ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።
 • ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ ከሜዳው ውጪ ከፍተኛ ግቦችን (27) ማስቆጠር የቻለው በኦልትራፎርድ ነው።
 • ዩናይትድ በሆዜ ሞሪንሆ የአሰልጣኝነት ዘመን በሁሉም ውድድሮች ባደረጓቸው 42 ጨዋታዎች በሜዳቸው ላይ ሽንፈት የገጠማቸው በመስከረም ወር 2016 ላይ በሲቲ የደረሰባቸው ብቸኛ ሽንፈት ነው። 

ማንችስተር ዩናይትድ

 • ዩናይትድ በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት 40 የነጥብ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አልገጠመው። ይህም በ1966 በማት በዝቢይ አሰልጣኝነት ዘመን ካስመዘገበው ክብረወሰን ጋር የሚስተካከል ነው።
 • የሆዜ ሞሪንሆው የመከላከል ክብረወስን በዚህ የውድድር ዘመን ምርጥ የሚባል ሲሆን፣ በዚህ የውድድር ዘመን ከተቆጠሩባቸው ዘጠኝ ግቦችም በኦልትራፎርድ መረባቸው የተደፈረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
 • ቀያይ ሰይጣኖቹ በሊጉ በሜዳቸው ያደረጓቸውን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን፣ ይህም በ11 ወራት ጊዜ ውስጥ ካደረጉት የውጤት ጉዞ ምርጥ የሚባል ነው።
 • ሞሪንሆ በሁሉም ውድድሮች ላይ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ባደረጋቸው 19 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በአራቱ ብቻ ነው (7 አቻ፣ 8 ሽንፈት)። ከዚህ መካከልም በፕሪሚየር ሊጉ ያሸነፉት በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው።
 • ጄሴ ሊንጋርድ ባለፈት 51 ጨዋታዎቹ በድምሩ ማስቆጠር ከቻላቸው ግቦች እኩል በሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ

 • ሲቲ በአንድ የውድድር ዘመን ያሸነፋቸው 13 ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሎች አርሰናል እና ቼልሲ ካስመዘገቧቸው የድል ክብረወሰኖች ጋር የሚስተካከል ነው። 
 • በኦልትራፎድ ድል ማደረግ የሚችሉ ከሆነ ደግሞ የተከታታይ ድላቸውን 14 አድርሰው ክብረወሰኑን በ2002 አርሰናል ካስመዘገበው ከፍተኛ ተከታታይ (በአንድ የውድድር ዘመን አይደለም) ድል ጋር የሚስተካከሉም ይሆናል።
 • ማንችስተር ሲቲ ካደረጋቸው 29 ጨዋታዎቹ ባለፈው ረቡዕ ብቻ በቻምፒዮንስ ሊጉ በሻከታር ዶኔትስክ ሽንፈት ገጥሞታል።
 • ሰርጂዮ አጉዌሮ ባለፉት ዘጠኝ የመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች ላይ በሙሉ ከሜዳው ውጪ ግብ አስቆጥሯል።
 • ኬቨን ደ ብሩኔ እና ዴቪድ ሲልቫ ስምንት የግብ ዕድሎችን በማመቻቸት የፕሪሚየር ሊጉን የግብ ዕድል የማመቻቸት ደረጃ እየመሩ ይገኛሉ።
Advertisements