ዌስትሀም ከ ቼልሲ / የቅድመ ጨዋታ ትንታኔ

ዌስትሀም በዴቪድ ሞየስ ስር ገና ማሸነፍን አሀዱ ብሎ ባይጀምርም ከሰሞኑ በሲቲ ለጥቂት የተሸነፈበት መንገድ ብዙ መሻሻሎች እንዳሳየ ጠቋሚ ነው። ነገርግን ካለበት የበዛ የጉዳት አሳሳቢነት እና ቼልሲ ወደዚህ የለንደን ደርቢ የሚመጣው በጥሩ አቋም ላይ ተገኝቶ ከመሆኑ አንፃር ሰማያዊዎቹ ትልቅ ግምት ያገኙበትን እንዲሁም ደግሞ ኸርናንዴዝ ወደሜዳ የሚመለስ ከሆነ የበዛ ትኩረት የሚያርፍበትን የዛሬ ቀትሩን ጨዋታ ሚኪያስ በቀለ እንደሚከተለው ቅደመ ዳሰሳ አድርጎበታል።


ኸርናንዴዝ ካለበት የጅማት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ እንዳገገመ ገና እርግጠኝነት ላይ ያልተደረሰ ቢሆንም ዌስትሀም የውድድር ዘመኑን ሶስተኛ እና ከመስከረም ወር ወዲህ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታ ድሉን ለማግኘት ቼልሲን በሚገጥምበት በዚህ ተጠባቂ የደርቢ ትንቅንቅ ላይ ወደሜዳ የሚመለስ ከሆነ ከሰማያዊዎቹ ጋር የሚያደርገው 14ኛ ጨዋታው ሲሆን ለመዶሻዎቹም ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆናቸው ይጠበቃል።

ሜክሲኳዊው ኮከብ እስካሁን ከቼልሲ ጋር ባደረገው 13 ጨዋታ ስምንት ግቦችን ማስቆጠር የቻለና በሰማያዊዎቹ ላይ የደመቀ ታሪክን ያስመዘገበ የመዶሻዎቹ ፊት አውራሪ ነው። በሌላ በኩል የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ካገኘው 32 ነጥብ 16 ያህሉን በሜዳው ቀሪውን እኩሌታ 16 ነጥብ ደግሞ ከሜዳው ውጪ በማሳካት በሜዳውና ከሜዳው ውጪ ሚዛናዊ ውጤት ያስመዘገበ የሊጉ ብቸኛው ቡድን ነው።

የጨዋታው ሰዓት: ቀትር 9:30

ቦታ : ለንደን ስታዲየም

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤት : ዌስትሀም 1 – ቼልሲ 2

ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት የሚያገኝበት የቴሌቪዥን ጣቢያ : ሱፐር ስፖርት፣ ቢቲ ስፖርት 1 (በመላው እንግሊዝ) እና ቤን ስፖርት (ለመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ)

የጨዋታው ዳኛ : አንቶኒ ቴይለር 

በዘንድሮው የውድድር ዘመን : ጨዋታ 9፣ ቢጫ 35፣ ቀይ 0፣ በአማካኝ በየጨዋታው 3.89 ካርዶች መዘዋል

                                ዌስትሀም 

ግምታዊ አሰላለፍ : አድሪያን፣ ራይስ፣ ኦግቦና፣ ዛባሌታ፣ ክሪስዌል፣ አንቶኒዮ፣ ፈርናንዴዝ፣ ኦቢያንግ፣ ማሱሀኩ፣ ላንዚኒ፣ ሳኮ 

ተቀያሪዎች : ሀርት፣ ትሮት፣ ባይራም፣ ሪድ፣ ጆንሰን፣ ሀስባኖቪች፣ ኖብል፣ ኩያቴ፣ ኪውና፣ አዩው፣ አርናቶቪች፣ ኸርናንዴዝ፣ ማርቲኔዝ

አጠራጣሪ : ባይራም (ዳሌ)፣ ኸርናንዴዝ፣ ኩያቴ፣ ሪድ (ሁሉም ጅማት)

ጉዳት : ካሮል (ጉልበት)፣ ኮሊንስ (ጅማት)፣ ፎንቴ (ቁርጭምጭሚት)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ድሽሽድሽሽ

ስነምግባር : ቢጫ 32 ቀይ 2

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ኸርናንዴዝ 4

የዴቪድ ሞየስ አስተያየት : “የአድሪናሊን ብቃት (ከማንችስተር ሲቲ ጋር በነበረውና ሀርት መሰለፍ ባልቻለበት ጨዋታ) ጥሩ ችግር እንደፈጠረብኝ መናገር እወዳለሁ። ምክንያቱም በዚህ ቡድን ውስጥ ለቦታ የሚደረግን ከባድ ፉክክር እየተመለከትኩ እገኛለሁ። 

“ማንም ከፈጣሪ የተሰጠ ምሉፅ የመጫወት መብት እንዳለው እንዲሰማው አልፈልግም። በዚህ ሰአት ቅዳሜ የትኛው እንደሚሰለፍ ይፋ አላደርግም። 

“ጆ የእንግሊዝ ተቀዳሚ ግብ ጠባቂ እንደሆነና በሚቀጥለው ክረምት የአለም ዋንጫ እንዳለም አውቃለሁ። ነገርግን እንደ ዌስትሀም አሰልጣኝ እኔ የሚያስደስተኝ ጨዋታዎችን ማሸነፍና ለዚህ ክለብ ጥሩ የሆነውን ነገር መምረጥ ነው።”  

                                   ቼልሲ

ግምታዊ አሰላለፍ : ኮርትዋ፣ አዝቤሉኬታ፣ ክርስቲንሰን፣ ካሂል፣ ሞሰስ፣ ባካዮኮ፣ ካንቴ፣ ፋብሬጋዝ፣ አሎንሶ፣ ሀዛርድ፣ ሞራታ 

ተቀያሪዎች : ካባሌሮ፣ ኤድዋርዶ፣ ሩዲገር፣ ፔድሮ፣ ኬኔዲ፣ ዊሊያም፣ አምፓዱ፣ ባትሱሀይ፣ ክላርክ ሳልተር፣ ሙሶንዳ 

አጠራጣሪ : ባካዮኮ (ጉልበት)፣ ዛፓኮስ (knock)፣ ባትሱሀይ (ለጨዋታ ብቁ ያለመሆን)

ጉዳት : ድሪንክወተር (ህመም)፣ ዴቪድ ሊውዝ (ጉልበት)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ድድድአድድ

ስነምግባር : ቢጫ 20 ቀይ 3

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሞራታ 9

የአንቶኒዮ ኮንቴ አስተያየት : “ይህ ሊግ በጣም አስቸጋሪ ነው። በተለይ ደግሞ ምክንያቱ በአሰደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኝ (ማንችስተር ሲቲ) ቡድን አለ። 

“ዌስትሀም ጥሩ ተጫዋቾች ያሉት ጥሩ ስብስብ አለው። እነሱን በዚህ ስፈራ (የደረጃ ሰንጠረዥ) መመልከት ትንሽ እንግዳ ነገር ነው።” 

Advertisements