ሴካፋ 2017 / ዋሊያዎቹ በይፋ ከሴካፋ ውድድር መሰናበታቸውን አረጋገጡ

በኬኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ 2017 የምስራቅ እና መካከለኛ የአፍሪካ ዋንጫ [ሴካፋ]ውድድር ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በይፋ ከውድድሩ ውጪ መሆኑን አረጋገጠ።

ዋሊያዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትኩረት እየተነፈገው እየሄደ በሚገኘው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ[ሴካፋ] ውድድር ላይ ተሳታፊ ቢሆንም ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ቡድኑ በብሔራዊ ቡድን ልምድ ያላቸው እና አዳዲስ ከሁለት ያልበለጡ ተጫዋቾች ከየክለቡ በመሰብሰብ በውድድሩ ላይ ተሳትፎ ደቡብ ሱዳንን አሸንፎ፣ በብሩንዲ ተሸንፎ፣ከዩጋንዳ ጋር ደግሞ አቻ ተለያይቶ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።

በተለይ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ዩጋንዳን ማሸነፍ የነበረት ቢሆንም በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በተቆጠረበት ጎል በአቻ ውጤት በማጠቀቁ በሂሳባዊ ስሌት እድሉ ባለመሟጠጡ ዛሬ የምድቡን ሌላኛው የደቡብ ሱዳን እና የብሩንዲ ጨዋታ ለመጠበቅ ተገዶ ነበር።

ዋሊያዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የውድድሩ ደካማ ቡድን የሆነችው ደቡብ ሱዳን ብሩንዲን ከ 3-0 በላይ ማሸነፍ ይጠበቅባት ነበር።ይህ ደግሞ የመሳካት እድሉ ጠባብ ቢሆንም ከውድድሩ ሙሉ ለሙሉ መሰናበታቸውን ለማረጋገጥ የዚህን ጨዋታ ውጤት መጠበቅ አስፈልጓል።

ዛሬ በተደረገው ጨዋታም ደቡብ ሱዳን ከ ብሩንዲ ጋር ያለጎል በአቻ ውጤት በማጠናቀቋ ዋሊያዎቹ በይፋ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አረጋግጠዋል።

ከነበሩበት ምድብ ሁለትም ዩጋንዳ እና ብሩንዲ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መሸጋገር ሲችሉ ደቡብ ሱዳን አንድ ነጥብ በማግኘት የምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ዋሊያዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደካማ ዞን በሚባለው ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ጋር እያስመዘገቡ ያሉት ውጤት አሳዛኝ ሆኗል።በቅርቡ እንኳን ማሸነፍ የቻሉት ጁቡቲን እና ደቡብ ሱዳንን መሆኑ ሲታወስ የብሔራዊ ቡድኑ የውጤት ቀውስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መናገር ይቻላል።

በተመሳሳይ በምድብ አንድ ኬኒያ እና ዛንዚባር ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ የቻሉ ቡድኖች መሆናቸው አረጋግጠዋል።

በዚህም መስረት በግማሽ ፍፃሜው

 ሀሙስ – ኬኒያ ከ ብሩንዲ

አርብ – ዩጋንዳ ከ ዛንዚባር ይጫወታሉ።

Advertisements