የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ከማንችስተር ደርቢ ጨዋታ በኋላ ስለተፈጠረው ክስተት መረጃ እያሰባሰበ ነው

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር የማንችስተር ዩናይትድ እና የማንችስተር ሲቲ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ከሁለቱ ክለቦች የፕሪሚየር ሊግ ደረቢ ጨዋታ በኋላ ተሳታፊ ስለነበሩበት የግርግርና የትርምስ መንስኤን ለማጠራት ምርመራ ጀምሯል።

እግርኳስ ማህበሩ ሲቲ እሁድ ምሽት በኦልትራፎርድ 2ለ1 ካሸነፈ በኋላ ለተፈጠረው ክስተት መረጃ ለማግኘት ከሁለቱም ክለቦች የምስክርነት መረጃ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል። የአመራር አካሉ የቅኝት ካሜራ ምስል ቅጂም እንዲሰጠው ሳይጠይቅ እንዳልቀረም ታምኗል።

የጨዋታው ዳኛ የነበሩት ማይክል ኦሊቨር በድህረ ጨዋታ ሪፓርታቸው ላይ ይህን ክስተት ባያካትቱትም ክስተቱን በስፍራው ሆኖ የተመለከተ አንድ ግለሰብ እንደተናገረው ከሆነ ግን ከፍ ያሉ ሙዚቃ ይሰማበት በነበረው የእንግዳው ክለብ የመልበሻ ክፍል በር ላይ 15 የሚሆኑ ሰዎች በግርግሩና በትርምሱ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ነገር ግን ምንም አይነት የተስነዝረ ጡጫ እንዳልተመለከተም ተናግሯል። 

ስለክስተቱ የተናገረው ግለሰብ የመልበሻ ክፍል ክስተቶችን በይፋ መናገር ህጉ ስለማይፈቅድለት ስሙ እንዳይጠቀሰም ዜናውን የዘግበው በቤል ሚዲያ ባለቤትነት የሚተዳዳረው ቲኤስኤን ድረገፅ ገልፅዋል።

ክስተቱ የተፈጠረው ፖሊሶችና የስተዲየም የጥበቃ አካላት በሚገኙበት የመልበሻ ክፍል መተላለፊያ ላይ ነበር።

Advertisements