ስለፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ምን ያህል ያውቃሉ?

ቅዳሜ በላ ሊጋው ሲቪያን 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት የረታው የዚነዲን ዚዳኑ ቡድን ከሌሎቹ የየአህጉራቸው ሻምፒዮኖች ጋር በዩናይትድ አረብ አመራትሷ አቡ ዳቢ ከተማ ላይ ለመፋለም እሁድ ወደሩቅ ምስራቅ አምርቷል።

ሪያል ማድሪድ በ2017 አራት ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ይሁን እንጂ ከዛሬ አንስቶ በዚህ ሳምንት በሚያደረጋቸው የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሽምፒዮንነቱን አምስት በማደረግ አሁንም ዓመቱን በተጨማሪ ስኬት ሊያጠናቅቅበት የሚችልበት ዕድል አለ።

ተከታዩ ፅሁፍም ስፖርትም ከፊፋ ዓመታዊ ውድድሮች መካከል አንዱ ስለሆነው ስለዚህ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሊያውቋቸው ይገባሉ ያለቻቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው በሰፊው ዳሳለች።

የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ምንድን ነው? 

የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ስድስቱ የፊፋ ኮንፌዴሬሽን (ዩኤፋ /አውሮፓ/፣ ኮንሜቦል /የደቡብ አሜሪካ/፣  ኤኤፍሲ /የእሲያ፣ የአፍሪካ፣ የሰሜን አሜሪካ፣ የመካከለኛው አሜሪካና ካሪቢያን/፣ እና የኦኤፍሲ /ኦሽኒያ/ ) ሻምፒዮኖች በዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚፋለሙበት ዓመታዊ ውድድር ነው።

ከየኮንፌዴሬሽኖቹ ሻምፒዮኖቹ በተጨማሪ፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫን አዘጋጅ የሚሆነው ሃገር የሊግ ሻምፒዮና የሚሆን ክለብም በውድድሩ ላይ ተጨምሮ በድምሩ ሰባት ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር ነው።

የውድድር ቅርፁ ምን ይመስላል?

የዓለም ክለቦች ሻምፒዮና የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው። ሰባት ክለቦች በውድድሩ ላይ ተሳታፊ እንደመሆናቸው ወደሩብ ፍፃሜው ለማለፍ የኦሽኒያ የእግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ሻምፒዮናው ክለብ ከአዘጋጅ ሃገሯ ሻምፒዮን ክለብ ጋር ለሩብ ፍፃሜው ለማለፍ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ያደርጋሉ።

በሩብ ፍፃሜው ውድድር የእሲያው ሻምፒዮን፣ የአፍሪካው ሻምፒዮን እና የሰሜን አሜሪካ፣ የመካከለኛ አሜሪካና ካሪቢያን ሻምፒዮኖች ቀደም ሲል በተደረገው ጥሎ ማለፍ ከቻለው ክለብ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

Real Madrid's players celebrating their FIFA Club World Cup last year

ሪያል ማድሪድ የባለፈው ዓመት የዚህ ውድድር አሸናፊ ነበር

በሩብ ፍፃሜው አሸናፊ የሆኑ ሁለት ክለቦች ከአውሮፓው ሻምፒዮን ወይም ከደቡብ አሜሪካው ሻምፒዮን ጋር በግማሽ ፍፃሜው የሚጫወቱ ይሆናል። በዚህ ዙር አሸናፊ የሚሆኑ ክለቦች ደግሞ ለፍፃሜ፣ ተሸናፊዎቹ ደግሞ ለሶስተኛ ደረጃ ይጫወታሉ።

በውድድሩ በየትኛውም ዙር ላይ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቁ ጨዋታዎች አሸናፊውን ለመለየት ወደተጨማሪ ሰዓትና የመለያ ምቶች እንዲያመሩ ይደረጋሉ።

ለዚህ ደረጃ የበቁ ክለቦች የትኞቹ ናቸው?

ሪያል ማድሪድ በቀጥታ ግማሽ ፍፃሜውን በመቀላቀል በጥሎ ማለፉ ላይ የኒውዚላንዱን ኦክላንድ ሲቲን እና በሩብ ፍፃሜው የጃፓኑን ኡራዋ ሬድ ዳይመንድስን የረታውን የዩናይትድ አረብ ኤመራቱን የፕሮ ሊግ ሻምፒዮን አል ጀዚራን ዛሬ (ረቡዕ) ምሽት ይገጥማል።

በግማሽ ፍፃሜው የኮፓ ሊበርታዶሬስ አሸናፊው የብራዚሉ ክለብ ግራሚዮ በሩብ ፍፃሜው የሞራኮውን ክለብ እና የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊውን ዊዳድ ካዛብላንካን በጭማሪ ሰዓት ያሸነፈውን የሜክሲኮውን ክለብ ፓቹካን ትናንት (ማክሰኞ) ምሽት ገጥሞ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የዓለም ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር የጨዋታ መርሃግብሮች

ማክሰኞ
3/4/10
ግራሚዮ
 ከ
ፓቹካ
በሃዛ ቢን ዚየድ ስታዲየም፣ አሊን  1-0
ረቡዕ
4/4/110
አል ጀዚራ
ከ 
ሪያል ማድሪድ
በዛየድ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም ምሽት 2፡00
ቅዳሜ
7/4/10
 ፓቹካ

ከአልጀዚራና ሪያል ማድሪድ አሸናፊ
በዛየድ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም፣ አቡ ዳቢ አመሻሽ
11.00
ቅዳሜ
7/4/10
ግራሚዮ

አልጀዚራና ማድሪድ አሸናፊ
በዛየድ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም፣ አቡ ዳቢ ምሽት 2፡00

የዓለም ክለቦች ዋንጫ መቼ ተጀመረ?

የዓለም ክለቦች ሻሚዮና ጅማሮ እ.ኤ.አ. ጥር 2000 ነበር። በ1999 ባየር ሙኒክን በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ 2ለ1 የረታው ማንችስተር ዩናይትድ የአውሮፓ ተወካይ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ዩናይትድ ለዚህ ውድድር ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ ለመጫወት ሲልም ራሱን ከኤፍኤ ዋንጫ ውድድር አድርጎ ነበር።

ውድድሩም አራት ቡድኖችን ያካተቱ ሁለት ምድቦች ኖሮት በምድብ ማጣሪያው እስከፍፃሜው ድረስ ክለቦቹ እርስ በእርስ ይፋለሙበት ነበር። በዚያ ውድድር ላይም ማንችስተር ዩናይትድ በቫስኮ ደጋማ 3ለ1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ውድድሩ እ.ኤ.አ. ከ2001-04 ድረስ አልተካሄድም። ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ. ከ2005 አንስቶ ሰባት ቡድኖች እየተሳተፉበት እስካሁን እየተካሄድ ይገኛል።

Advertisements