የ2018 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ተለይተው ታወቁ

የ2018 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ዛሬ በግብፅ ካይሮ ይፋ ሲሆኑ ኢትዮጵያን የሚወክለው ቅዱስ ጊዮርጊስም ተጋጣሚውን አውቋል።

59 ክለቦች በማጣሪያ ጨዋታ ላይ የሚሳተፉበት እና ወደ ምድብ ድልድሉ የሚያልፉ 16 ቡድኖችን ለመለየት የሚደረገው የ2018 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል።

2007 ላይ አሸናፊ የነበረው ኢቶይል ዱ ሳህል፣የ 2016 አሸናፊው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣የ2017 አሸናፊው ዊዳድ ካዛብላንካ፣በ2017 ለዋንጫ ደርሶ የነበረው አል አህሊ እንዲሁም የ2018 የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊው ቲፒ ማዚምቤ የመጀመሪያውን ዙር አልፈው ከሁለተኛ ዙር ጀምሮ ጨዋታቸውን ማድረግ ይጀምራሉ።

ከሁለት የማጣሪያ ጨዋታ በኋላ 16 ቡድኖች ወደ ምድብ ድልድል የሚቀላቀሉ ሲሆን በሁለተኛው ዙር የሚሸነፉ ቡድኖች ደግሞ ወደ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

ዜስኮ ዩናይትድ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ባለፉት አመታት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆኑ ዛምቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ክለቦች ትወከላለች።ዜስኮ እና ዜናኮም ዛምቢያን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል።

ኢትዮጵያን የሚወክለው ቅ/ጊዮርጊስ ደግሞ በመጀመሪያው ዙር ከ ደቡብ ሱዳኑ አል ሳላም ጋር የሚጫወት ይሆናል።ይህን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ እና ከማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒ ኤስ ጋር የሚጫወት ይሆናል።

ፈረሰኞቹ ጥሩ ድልድል የደረሳቸው ቢሆንም ማለፍ የሚችሉ ከሆነ በሁለተኛው ዙር ግን ከመጀመሪያው ዙር በተሻለ በአንፃራዊ  ጠንከር የሚል ቡድን ይገጥማል።

በተለይ የዩጋንዳው ኬሲሲኤ ከ2017 የቻምፕየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ለመግባት ከ2016 አሸናፊው ማሜሎዲ ሰንዳውንን ጋር ተጫውቶ ስምንት ደቂቃ ሲቀረው በተቆጠረበት ጎል መውደቁ ሲታወስ ኬሲሲኤ ሊናቅ የሚችል ቡድን እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል።

የወቅቱ አሸናፊው ዊዳድ ካዛብላንካ በበኩሉ በሁለተኛው ዙር ላይ ከማሊው ስታድ ዴ ማሊያን እና ከአይቮሪኮስቱ ዊልያምስቪል አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ተጋጣሚዎች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በፈረንጆች ከየካቲት 9 እስከ 11 የሚያደርጉ ይሆናል።

ሙሉ ተጋጣሚዎቹን ከምስሉ ይመልከቱ

ምስል – ከክለቡ ገፅ የተወሰደ

Advertisements