ሴካፋ 2017 / ኬንያ ብሩንዲን በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ [ሴካፋ] የግማሽ ፍፃሜ አንድ ጨዋታ በኬንያ እና በብሩንዲ መካከል ተደርጎ ባለሜዳዎቹ ወደ ፍፃሜ ማለፉቸው አረጋግጠዋል።

<!–more–>

በኬንያ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ 2017 የሴካፋ ውድድር በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ “ሀራምቤ ስታርሶቹ”ኪሱሙ ላይ ብሩንዲን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፈዋል።

በተመልካች ድርቅ የተመታው ውድድር ባለሜዳዎቹም ቢሆን በሀገራቸው ጠንካራ ድጋፍ ማግኘት አልቻሉም።ሙሉ ለሙሉ ሊያስብል በሚችል መልኩ ውድድሩ በባዶ ስተድየም መካሄዱን ቀጥሏል።

በዛሬው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኬኒያዎች ደካማ አጀማመር በማድረጋቸው ብሩንዲዎች ጎል ለማስቆጠር ተቃርበው ነበር።

በተለይ 13ኛ ደቂቃ ላይ ሻባን ሁሴን ከቅጣት ምት የተላከውን ኳስ በጭንቅላት ገጭቶ አንግል የገጨበት ብሩንዲዎች ከሞከሯቸው አስደንጋጭ ሙከራዎች ውስጥ ይጠቀሳል።

ኬኒያና ብሩንዲ ለመሸናነፍ 90 ደቂቃው በቂ አልሆነላቸውም።በጭማሪው 97ኛ ደቂቃ ላይ የሊዮፓርዱ አማካይ ኢሱዛ በግራ እግሩ የመታው ኳስ የጨዋታው ብቸኛ ጎል ሆኖ ተቆጥሮ ኬንያ ወደ ፍፃሜ እንድታልፍ አስችሏታል።

በሌላ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዩጋንዳ እና ዛንዚባር ነገ የሚጫወቱ ሲሆን አሸናፊው ቡድን ከኬኒያ ጋር ለፍፃሜ ይጫወታል።

Advertisements