አርሰን ቬንገር ለዋንጫ ፉክክሩ እጅ እንደማይሰጡ ተናገሩ

የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ቬንገር ምንም እንኳ አርሰናል ረቡዕ ምሽት ከዌስት ሃም ጋር ያደረገውን ጨዋታ ያለምን ግብ በአቻ ውጤት በማጠናቀቁ ከመሪው ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው ልዩነት ወደ19 ነጥቦች ቢያድግም የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ለሚደረግው ፉክክር ግን ተስፋ እንደማይሰጡ ገልፀዋል።

“ስለዚያ መናገር አልፈልግም። ርዕሰ ጉዳይ ለመፍጠር ጥሩ ይሆናል። ነገር ግን እኛ ቀጣዩ ጨዋታ ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል። እና ደግሞ ስለዋንጫው ለማውራት ሲቲ ገና ብዙ ይቀረዋል።

“ነገር ግን ርቆ መገኘት እና ተስፋ መቁረጥ ለየቅል ናቸው። ተስፋ አትቁረጥ። ስራችን የምንችለውን ያህል መፋለምና የተሻለውን ማድረግ ነው። በሌላ ነገር ላይ አብዘተን ትኩረት ማደረግ አይኖርብንም።

“መፋለም አለብን። ሥራችን መፋለም እና ሁሉንም ነገር በማድረግ መቀጠል ነው። ከዚያ የት እንደምንደርስ እንመለከታለን። ሲቲ ሲቲ ነው። ምን እየሆነ እንዳለ በሚገባ ታውቃላችሁ። በሊጉ እንደማንኛውም [ክለብ] ከሲቲ ጋር ያለውን ችግር ተጋፍጠናል።” ሲሉ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግረዋል።

ቬንገር ይህን ቢሉም፣  አርሰናል በአራተኛ ደረጃ ከሚገኘው ቶተንሃም በአንድ ነጥቦች ዝቅ ብሎ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ከመሪው ሲቲ ደግሞ በ19 ነጥቦች ዝቅ ብሎ መገኘቱ ከዋንጫ ፉክክሩ የወጣ ይመስላል። የበላይ አራት ደረጃ ውስጥ ለመግባትም ካሉት ተፋካካሪ ክለቦች ብዛት አንፃር ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል። 

Advertisements