“እግርኳስ ብድር እንደሚከፍል ተስፋ አለኝ።” – መሲ

በ2014 የዓለም ዋንጫ ሃገሩ አርጄንቲና በጀርመን ሽንፈት የደረሰባት የባርሴሎናው ኮከብ ሊዮኔል መሲ “እግርኳስ ብድር ከፋይ” በመሆኑ ክፍያውን በክረምቱ የዓለም ዋንጫ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጓል።

የ30 ዓመቱ አርጄንቲናዊ ተጫዋች የሪዮ ዴጄኒየሮው ሽንፈት ስሜት አሁንም ድረስ  እንደሚሰማው አምኖ ወቅታዊው የአርጄንቲና ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ጆርጌ ሳምፓውሊ እግርኳስ ውለታ መላሽ እንደሆነች በሰጡት ሃሳብ ላይ እንደሚስማማ ተናግሯል።

“እግርኳስ ብድር እንደሚከፍል ተስፋ አለኝ።” ሲል መሲ ከፊፋ ድረገፅ ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ገልፅዋል።

“ጆርጌ ሳምፖውሊ የተናገረውን ሰምቻለሁ። እርግጥ ራሱ አልናገረኝም።

“በ2014ቱ ፍፃሜ በጀርመን የደረሰብም ሽንፈት ህመም ፈፅሞ የሚድን አይመስለኝም። የሆነውን ነገር ባለበት መርሳት የሚኖርብኝ ይመስለኛል። ሁልጊዜም ግን ባለበት ይኖራል።

“የዓለም ዋንጫ ጥሩ ትዝታዎችን ይፈጥራል። ነገርን የሚያሙ ትዝታዎችንም ጭምሮ ነው።” 

አርጄንቲና የፊታችን ሰኔ ወር በሚካሄደው የሩሲያው ዓለም ዋንጫ በምድብ ዲ ከአይስላንድ፣ ክሮሺያ እና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላለች።

Advertisements