ሴካፋ 2017/ ዛንዚባር ዩጋንዳን በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች

በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2017 የሴካፋ ውድድር ዛንዚባር ዩጋንዳን በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሷን አረጋገጠች።

በኬኒያ ኪሱሙ በሞይ ስታድየም የተደረገው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛንዚባር የ2015 የውድድሩን አሸናፊ የሆኑትን ዩጋንዳን 2-1 በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሰዋል።

ዛንዚባሮች አብዱላዚዝ ማካሜ በ 22ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል መሪ መሆን ቢችሉም ዴሪክ ንሲምባምቢ የአቻነቷን ጎል ለክሬንሶቹ ማስቆጠር ችሏል።

ከእረፍት መልስ 57 ኛ ደቂቃ ላይ መሀመድ ኢሳ ያስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ዛንዚባሮችን አሸናፊ አድርጓል።

በዚህም መሰረት እሁድ በማቻኮስ ኬንያታ ስታድየም ከኬንያ ጋር ለፍፃሜ የሚጫወቱ ይሆናሉ።

Advertisements