ክሎፕ፣ ናቢ ኪየታ ሊቨርፑልን በጥር ወር ለመቀላቀል ተስሟምቷል መባሉን አስተባበሉ

የርገን ክሎፕ ጊኒያዊው አማካኝ ናቢ ኪየታ በጥር ከጀርመኑ ክለብ አርቢ ሌፕዚግ ወደሊቨርፑል የሚዛወር ስለመሆኑ የቀረበውን ሪፖርት አስተባብለዋል።

ባለፉት ቅርብ ጊዜያት የተዘገቡ የጭምጭምታ ወሬዎች ጊኒያዊው ተጫዋች ወደአንፊልድ የመዛወሩ ጉይ እርግጥ እንደሆነ ቢገልፁም ሊቨርፑል ከቦርንማውዝ ጋር ለሚያደረገው የእሁዱ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ክሎፕ ግን ዘገባውን አስረግጠው አስተባብለዋል።

ኪየታ በዚህ የውድድር ዘመን ቀዮቹን ይቀላቀል እንደሆን ለቀረበላቸው ጥያቄ ክሎፕ “አይቀላቀልም። እሱ የሌፕዚግ ተጫዋች ነው። 

“በዚህ ሁኔታ ላይ ደግሞ እንዴት ስምምነት እናደርጋለን? ስለዝውውሮች የተናገርንም አይመስለኝም።

“እሱ በሰኔ ወይም በኃምሌ ወደሊቨርፑል የሚመጣበት ስምምነት ከክለቡ ጋር አለን። 

“ስለዚያ ደግሞ የምንለው ነገር የለንም። ስለዚህም [እሡን ስለማዛወር] አናስብም። ምክኒያቱም ሁሉም ነገር የሚሆነው ሌፕዚጎች የተናገሩት ብቻ ነው።

“እነሱ ደግሞ [በቅርቡ] ምንም የሚሸጥ ተጫዋች እንደሌላቸው ተናግረዋል። ታዲያ እንዲህ አይነት ነገር ለምን ያደርጋሉ?

“ስለዚህ እኛም ስለዝውውሩ አናስብበትም።” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

Advertisements