ሪያል ማድሪድ በሮናልዶ ብቸኛ ግብ የዓለም ክለቦች ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

ሪያል ማድሪድ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቅዳሜ በአቡ ዳቢ በተደረገው የዓለም የክለቦች ዋንጫ የብራዚሉን ክለብ ግራሚዮን 1ለ0 በመርታ በ2017 አምስተኛ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የዓለም ክለቦች ዋንጫን ያነሳው የዚነዲን ዚዳኑ ሪያል ማድሪድ በውድድሩ ታሪክ ዋንጫውን በማንሳት ስኬት ከሃገሩ ክለብ ባርሴሎና መስተካከል ከመቻሉም ባሻገር እየተጠናቀቀ በሚገኛው የፈረንጆቹ ዓመት ማንሳት ከቻላቸው የ ላ ሊጋ፣ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫዎች በተጨማሪ ይህ አምሰተኛ ዋንጫው ሊሆንለት ችሏል።

ለሪያል ማድሪድ ለዚህ ውጤት መብቃት ደግሞ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበረው አሁንም በሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ ስምንተኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ብቸኛ ግብ ከቅጣት ምት ማስቆጠር የቻለው የባሎን ዶር አሸናፊው ፖርቱጋላዊው ኮከብ ነበር።

Advertisements