ስድስተኛው የፕሪሚየር ሊጉ ተሰናባች አሰልጣኝ በስንብት ደጃፍ ላይ ናቸው

እንደቶክስፖርት ዘገባ ከሆነ የስቶክ ሲቲው አሰልጣኝ ማርክ ሂዩዝ ፖተርሶቹ ቅዳሜ ከቀትር በኋላ በዌስት ሃም የ3ለ0 ሽንፈት የደረሰባቸው መሆኑን ተከትሎ በክለቡ የሚኖራቸውን ስራ ለመታደግ ከክለቡ የሁለት ጨዋታዎች ዕድል ብቻ ተሰጥቷቸዋል። 

ስቶክ በፕሪሚየር ሊጉ ባዳረጋቸው 18 ጨዋታዎች ለመጨረሻ ጊዜ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ በመሸነፍ 16 ነጥቦችን ሰብስቦ በደረጃ ሰንጠረዡ በ17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሽንፈትም ከፖተርሶቹ (10) በላይ ብዙ ሽንፈት የገጠማቸው ኒውካሰል እና ስዋንሲ ሲቲ (11) ብቻ ቢሆኑም፣ ብዙ ግብ (39) መረባቸው ላይ እንዲያርፍ በማድረግ ግን የሚስተካከላቸው የለም።

በዚህም ምክኒያት የሂዩዝ የአሰልጣኝነት መንበር አደጋ ላይ ይገኛል። የስቶክ ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ዌስትሃም እና ዌስት ብሮምዊች አልቢዮን ሲሆኑ በእነዚህ ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ የሚያስመዘግቡት ደካማ ውጤት ዳግሞ የ54 ዓመቱን አሰልጣኝ ስራ የሚያሳጣ ይሆናል።

በ2013 ግንቦት ወር ክለቡን ለማሰልጠን የተቀጠሩት ሂዩስ ካለፈው ዓመት መጥፎ የሚባል ውጤት ውጪ ስቶኮችን ለሶስት የውድድር ዘመናት በደረጃ ሰንጠረዡ ከወገብ በላይ በማጠናቀቅ እንዲጨርሱ ማድረግ ችለዋል።

Advertisements