ዌስትብሮም ከ ማንችስተር ዩናይትድ / የቅድመ ጨዋታ ትንታኔ

ቀያዮቹ ሴይጣኖች በዘንድሮው የውድድር ዘመን በኦልትራፎርድ ማግኘት ከነበረባቸው 27 ነጥብ 24 ያህሉን ማሳካት ችለው በሜዳቸው ጥንካሬያቸውን ቢያሳዩም ከሜዳቸው ውጪ ማግኘት ከነበረባቸው 24 ነጥብ 14 ያህሉን ብቻ ማግኘታቸው በአለን ፓርዲው ስር ከገቡበት ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ማግኘት ቀርቶ ጎል ማስቆጠር ከተሳናቸው እንዲሁም ደግሞ በአንድ የውድድር ዘመን 20 ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ከብዷቸው ካስመዘገቡት የ 1971 አሳፋሪ ክብረወሰናቸው በኋላ ትልቁ የሚባለውንና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለ 17 ጨዋታ ግብ ያለማስመዝገብ አሳፋሪ ድግግሞሽ ላይ ለመድረስ የዛሬው ጨዋታ ላይ ግብ አለማስቆጠር ብቻ የሚጠበቅባቸው ባጊሶች እየተንተፋተፉም ቢሆን በሜዳቸው ለዩናይትድ በቀላሉ እጅ ላለመስጠት እንደሚጥሩ ይጠበቃል። ይህን የኦልትራፎርዱ ክለብ ከሜዳው ውጪ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ባለሜዳው ዌስትብሮም በበኩሉ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር የጎል ድርቁን ለመፍታት እና የመጀመሪያ ነጥቡን ለማግኘት እንዲሁም የቀደመ አሳፋሪ ታሪኩን ለመሻር የሚያደርጉትን ትንቅንቅ የኢትዮአዲሱ ሚኪያስ በቀለ እንደሚከተለው ቅድመ ዳሰሳ አድርጎበታል።


የጨዋታው ሰዓት : አመሻሽ 11:15

ቦታ : ሀውቶርን ስታዲየም

ያለፈው የውድድር ዘመን ውጤት : ዌስትብሮሚች አልቢየን 0 – ማንችስተር ዩናይትድ 0

ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት የሚያገኝበት የቴሌቪዥን ጣቢያ : ሱፐር ስፖርት፣ ቢቲ ስፖርት 1 (በመላው እንግሊዝ) እና ቤን ስፖርት (ለመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ)

የጨዋታው ዳኛ : አንቶኒ ቴይለር 

በዘንድሮው የውድድር ዘመን : ጨዋታ 11፣ ቢጫ 42፣ ቀይ 0፣ በአማካኝ በየጨዋታው 3.81 ካርዶች መዘዋል

                      ዌስትብሮሚች አልቢየን

ግምታዊ አሰላለፍ : ፎስተር፣ ኢቫንስ፣ ሄጋዚ፣ ጊብስ፣ ኒዮም፣ ባሪ፣ ሊቨርሞል፣ ክራሽቾያክ፣ ሮብሰን-ካኑ፣ ማክሌን፣ ሮንዶን 

ተቀያሪዎች : ማይሂል፣ በርክ፣ ፊሊፕስ፣ ማኩሌይ፣ ብሩንት፣ ሮድሪጌዝ፣ ፊልድ፣ ያኮብ፣ ፊሊፕስ፣ ቻዲል 

አጠራጣሪ : ባሪ (ብሽሽት)፣ ቻዲል፣ ጄምስ ሞሪሰን (ሁሉም ጅማት)

ጉዳት : ዳውሰን (ጉልበት)፣ ሞሪሰን (ጅማት)

ቅጣት : የለም

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ሽአአአሽአ

ስነምግባር : ቢጫ 38 ቀይ 1

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሮብሰን ካኑ፣ ሮድሪጌዝ፣ ሮንዶን 2

​የአለን ፓርዲው አስተያየት : “ጨዋታዎችን ማሸነፍ እንዳለብን ጫና ያለብን ሲሆን ያንን እሁድ የሚሳካ ከሆነ ሁሉም ነገር የተሻለና ጥሩ ይሆናል።

“ከጨዋታው በፊት ነጥብ አገኝ ይሆን? ሊሆን ይችላል። ነገርግን ሁሉ ነገር የሚወሰነው በጨዋታው ላይ በሚኖረው ሂደት ነው።

“ጉጉት አሳይተናል። አውቶብስ የምናቆም አይደለንም። ለማጥቃት ጥረት የምናረግ ስንሆን ከሊቨርፑል ጋርም ጥሩ ነገር መስራት ችለናል። ከዛ ጨዋታም ከዩናይትድ ጋር ለሚኖረን ፍልሚያ መነሳሻ ልንወሰድ እንችላለን።”          

                    ማንችስተር ዩናይትድ

ተጠባቂ አሰላለፍ : ዴይኻ፣ ስሞሊንግ፣ ጆንስ፣ ያንግ፣ ቫሌንሲያ፣ ማቲች፣ ሄሬራ፣ ራሽፎርድ፣ ሊንጋርድ፣ ማርሻል፣ ሉካኩ

ተቀያሪዎች : ፔሬራ፣ ሮሜሮ፣ ካሪክ፣ ቱአንዜቤ፣ ሊንድሎፍ፣ ማታ፣ ማክቶምናይ፣ ሚሼል፣ ዳርሚያን፣ ብሊንድ፣ ሾው፣ ኢብራሞቪች፣ ማኪቴሪያን፣ ሮሆ፣ ፌላኒ

በጨዋታው ላይ መሰለፋቸው የሚያጠራጥር : ካሪክ (ለጨዋታው ብቁ ሆኖ ከመገኘት ጋር በተያያዘ)፣ ፌላኒ (ጉልበት)፣  ሮሆ (ጭንቅላት)

ጉዳት : ቤሊ (ብሽሽት)

ቅጣት : ፖል ፖግባ

የቅርብ ጊዜ ውጤት : ድድድድሽድ

ስነምግባር : ቢጫ 26፣ ቀይ 1

መሪ ግብ አስቆጣሪ : ሉካኩ 9

የጆሴ ሞውሪንሆ አስተያየት :  “ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነን። በሌላው የውድድር ዘመን ቢሆን ያለን ነጥብ በአንደኛነት የሚያስቀምጠን ነበር። አዎ! ነገርግን ሁለተኛ ነን።

“ቀድሜ እንደተናገርኩት ከጨዋታ ጨዋታ ባለው ሂደት በሰአቱ በምናደርገው አንድ ጨዋታ ላይ ትኩረት እናድርግ። በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ምንላይ እንደምንገኝ እንመልከት። 

“እነሱ ልምድ ያላቸው፣ በአካል ብቃት የዳበሩና ፕሪምየር ሊጉን የሚያውቁ ተጫዋቾች አሉዋቸው። የእነሱ ስብስብ እና ፍላጎት ጥሩ ነው። ጨዋታው አስቸጋሪ ይሆናል።” 

Advertisements