ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲን የማሰልጠን ስራ ያቀለለት ደ ብሩይኔ እንደሆነ ገለፀ

ፔፕ ጋርዲዮላ አማካኝ ተጫዋቹ ኬቨን ደብሩይኔን አወድሶ የተጫዋቹ ከኳስ ውጪ ጭምር የሚያደረገው እንቅስቃሴ የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝነት ስራውን እንዳቀለለት ገልፅዋል።

ሲቲ ቅዳሜ ምሽት በኢትሃድ ስታዲየም ቶተንሃምን 4ለ1 በሆነ ውጤት በረታበት እና 16ኛ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን በማጣጣም የደረጃ ሰንጠረዡን በ14 ነጥቦች ልዩናት መምራት በቻለበት ጨዋታ ደ ብሩይኔ አስደናቂ ብቃት ማሳየት ችሏል።

አይካይ ጉንዶጋን በ14ኛው ደቂቃ የጨዋታውን የመጀመሪያ ግብ ለሲቲ በግምባሩ ገጭቶ ካስቆጠረ በኋላ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ደግሞ የጨዋታው ማሳረጊያ ሁለት ግቦችን ራሂም ስተርሊንግ ከቅርብ ርቀቶች ላይ ማስቆጠር ችሏል። ይሁን እንጂ ለሲቲ ከሁሉ በላይ ወሳኝ የነበረችዋን ሁለተኛ ግብ በ70ኛው ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ማሳረፍ የቻለው ከጨዋታው በኋላ ከአሰልጣኙ ከፍ ያለ አድናቆት የተቸረው ደ ብሩይኔ ነበር።

“ያለኳስ በአንድ ቡድን ላይ ብልጫ መውሰድ ጥንካሬነትና ጥሩነት ነው።” ሲል ጋርዲዮላ ለቢቲ ስፖርት ተናግሮ አክሎም “እነሱ ጥሩ ጥራት ነበራቸው። ነገር ግን እኛ ከፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነውን ለመርታት ጥሩ ጨዋታ አድርገናል።

“ዛሬ ኬቨን ደ ብሩይኔ ያደረገውን አይናት ብቃት መመልከት እንደቻላችሁት ብልህ ቡድን ነው ያለን። እሱ [ደ ብሩይኔ] ከኳስ ጋር ምን ያህል ጥሩ እንደሚጫወት ማለም እንኳ ይከብዳል። ነገር ግን ምን ያህል እንደሚንቀሳቀስም ልትመለከቱትም ትችላላችሁ።

“በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ እንደሚሮጥ ምርጥ ተጫዋች ሌሎች ተጫዋቾችም እንዲታዩ ዕድል ፈጥሮልናል። ይህ ሲሆን ደግሞ ለክለቡ አሰልጣኝ ክለቡን ማሰልጠን ቀላል ያደርግለታል።” በማለት ተናግሯል።

Advertisements