የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

በ18ኛው ሳምንት ከተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሃግብሮች መካከል በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ አምስት ጨዋታዎች ላይ በሙሉ ሽንፈት ቢደርስበትም ሮይ ሆጂሰንን አሰልጣኝ አድርጎ ከቀጠረ በኋላ ከ13 ጨዋታዎች 17 ነጥብ በመሰብሰብ እና በሰባት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ያልገጠመው ክሪስታል ፓላስ ሌስተር ሲቲን የረታበት ጨዋታ ድንቅ ነበር።

ተከታዩ ፅሁፍም በዘ ቴሌግራፉ ድረገፅ ምርጫ በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለክለቦቻቸው ውጤታማነት ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋቾች ናቸው ያላቸውን 11 ምርጥ ተጫዋቾች እንደሚከተለው ተመልክቷል።

ማቲው ሪያን፣ ግብ ጠባቂ

ከበርንሌይ ጋር በተደረገው አስቸጋሪ ጨዋታ ግብ ጠባቂው ለብራይተን ከአጥቂው ክሪስ ዉድ እና ከስኮት አርፊልድ የተሞከሩበትን ድንቅ የግብ ሙከራዎች ማምከን ችሎ የክለቡ መረቡን ሳያስደፍር መውጣት ችሏል።

ካይል ዎከር፣ ቀኝ ተከላካይ

ለቶተንሃሞች ከሜዳቸው ውጪ በማንችስተር ሲቲ መሸነፉ ብቻውን ጉዳት እንዲሰማቸው በቂ ቢሆንም፣ ከዚህ በላይ ከባድ የሆነባቸው ግን የቀድሞው የቀኝ መስመር ተከላካያቸው በሜዳው ላይ የበላይነትን ያሳየበት አስገራሚ ብቃቱ ነበር።

ዛንካ፣ የመሃል ተከላካይ

ዛንካ ወይም በሙሉ ስሙ ማቲያስ ዮርገንሰን ይባላል። ተጫዋቹ በቪካሬጅ ሮድ ከዋትፎርድ ባደረጉት ጨዋታ በኸደርስፊልድ የመሃል ተከላከይ ክፍል ላይ ከክርስቶፈር ሺንድለር ጋር ድንቅ የሚባል ጥምረት ማሳየት ችሏል።

ደዣን ሎቭረን፣ የመሃል ተከላካይ

የሊቨርፑል ተከላካይ ባልተለመደ መልኩ ግብ ከማስቆጠሩም በላይ የየርገን ክሎፑ የተከላካይ ክፍል በተቺዎቹ የሚሰነዘርበትን ድክመት ሳያሳይና መረቡን ሳያስደፍር ከሜዳው ውጪ ቦርንማውዝን በማሸነፍ ምን ያህል አቅም እንዳለው ማሳየት ችሏል። 

አርተን ማሱዋኩ፣ የግራ ተከላካይ

ማሱዋኩ በዌስት ሃም የግራ ክንፉን በመምራትና ስቶክ ሲቲን ማሸነፍ እንዲችሉ በማድረግ ስመጥር ተጫዋች ለመሆን ብዙ ጊዜ ያልወሰደበት ተጫዋች ነው። በጨዋታው ላይም ምን ያህል ከፍ ያለ ፋይዳ ያለው ተጫዋች እንደሆነም ማስመስከር ችሏል።

ኬቨን ደብረይኔ፣ የቀኝ አማካኝ

ዴቪድ ሳልቫ በጨዋታው ላይ ያለመሰለፉ ማንችስተር ሲቲ በቶተንም ላይ የበላይናቱን በወሰደበት ጨዋታ ደብሩይኔ ኃላፊነቱን በሚገባ መወጣት ችሏል። ቶተንሃሞች እሱን በነፃነት ሊተዉት ባለመቻላቸውም መጥፎ የሚባሉ ጥፋቶችን ሲፈፅሙባት ታይተዋል።

አሮን ሙይ፣ የመሐል አማካኝ

አውስትራሊያዊው አማካኝ ያደረጋቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የኳስ ቁጥጥሮች ሁልጊዜም እሱ የበላይ በሚሆንባቸው ጨዋታዎች ላይ እንደሚያሳዩት ኸደርስፊልዶች ጥሩ መጫወት ችለዋል። ተጫዋቹ ዋትፎርድን እንዲያሸንፉም አሁንም ለክለቡ ግብ ማስቆጠር ችሏል። 

መሱት ኦዚል፣ የመሃል አማካኝ

አርሰናል በጠባብ ግብ ኒውካሰልን ያሸነፈበት ጨዋታ ምርጥ ብቃቱን ማሳየት ከቻለበት የውድድር ዘመኑ ጨዋታዎች መካከል አንዱ እንደሆነ መናገር ቢቻልም፣ ነገር ግን ኦዚል በዚህ ጨዋታ ለማድፈኞቹ ብቸኛውን ግብ ያስቆጠረበት መንገድ ያለውን ደረጃውን የጠበቀ አጨዋወት ማሳየት የቻለ ነበር።

ማኑኤል ላንዚኒ፣ የግራ አማካኝ

ዌስት ሃም ከስቶክ ሲቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ የመጀመሪያዋ ወሳኝ ግብ እንድትቆጠር ላንዚኒ የፍፁም ቅጣት ምት ያገኘበት መንገድ አወዛጋቢ ቢሆንም፣ ነገር ግን አርጄናቲናዊው ድንቅ ተጫዋች በጨዋታው ላይ ያሳየውን ብቃት ማንም አይጠራጠርም። እንደእሱ አይነት ብቃት ያለው ተጫዋች ግን ከዚህም ባላይ ገና ብዙ ማድረግ ግን ይጠበቅበታል።

ዊልፍሬድ ዛሃ፣  የፊት ተጫዋች

ለእንግሊዝ እግርኳስ የእግር እሳት ሊሆን የሚችል አንድ ጉዳይ ቢኖር ዛሃ ለእንግሊዝ ከመጫወት ይልቅ ለአይቮርኮስት መጫወትን መምረጡ ነው። የክሪስታል ፓላሱ የፊት ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን ልዩ ችሎታውን ያሳየ ሲሆን፣ ሌስተር ሲቲን ሲያሸንፉ ያሳየው እንቅስቃሴ እና ክህሎት ዳግሞ ድንቅ ነበር።

መሐመድ ሳላህ፣ አጥቂ

የሊቨርፑሉ የፊት ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን 20 ግቦችንን በመረብ ላይ በማሳረፍ ወደእንግሊዝ እግርኳስ ዳግም ከተመለሰበት የክረምቱ ወቅት አንስቶ አስገራሚ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ሳለህ ብዙ ጊዜ በማይከሰተውና እሱ በማያስቆጠርባቸው ነገር ግን ጥሩ ጥምረትና ብቃት ባሳየባቸው ጨዋታዎች ላይ ኳስና መረብን ሳያገኛኝ ሲወጣ መመልከትም በእጅጉ የሚያስገርም ነገር ነው።

የ18ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ 11 የቡድን ስብስብ  አሰላለፍም ይህን ይመስላል
Advertisements