ፖሊስ በስተርሊንግ ላይ በደረሰው የዘረኝነት ጥቃት ላይ ምርመራ እንደሚከፍት ገለፀ

የግሬተር ማንችስተር ፖሊስ ቅዳሜው ከቶተንሃም ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ በማንችስተር ሲቲው ተጫዋች ራሂም ስተርሊንግ ላይ ደርሷል ተብሎ በተዘገበው የዘረኝነት “የጥላቻ ወንጀል” ጥቃት ላይ ምርመራ ከፍቷል።

ስተርሊንግ ሲቲ ቶተንሃምን 4ለ1 ማሸነፍ በቻለበት እና 16ኛ ተከታታይ የሊግ ድሉን አጣጥሞ የደረጃ ሰንጠረዡን በ11 ነጥቦች መምራት በቻለበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ይሁን እንጂ ከጨዋታው በኋላ ስተርሊግ በሲቲ የልምምድ ሜዳ መግቢያ ላይ የዘርኝነትና በእግር የመረገጥ ጥቃት እንደረሰበት የሚገልፁ ዘገባዎች ወጥተዋል።

ከጨዋታው በኋላ የደረሰውን ነገር የሚያውቀው ክለቡ ግን አቤቱታትውን ለፖሊስ አላቀረበም። 

ሆኖም የማንችስተር ከተማ ፓሊስ ግን በ”ጥላቻ ወንጀል” ጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚከፍት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ገልፅዋል።

Advertisements