አትሌቲኮ ማድሪድ በግሪዝማን ጉዳይ በባርሰሎና ላይ ለፊፋ አቤቱታ ሊያቀርብ ነው

አትሌቲኮ ማድሪድ በግሪዝማን የዝውውር ጉዳይ በባርሴሎና ላፕ ለዓለም አቀፉ እግርኳስ አመራር አቤቱታ ሊያቃርብ እንደሆነ የስፔኑ ጋዜጣ አስ ዘግቧል።

የማድሪዱ ክለብ አቤቱታ የባርሴሎና የስራ አስፈፃሚ የሆኑት ጉሌርሞ አሞር በሳምንቱ መጨረሻ ባርሴሎና በፈረንሳያዊው ተጫዋች ዝውውር ጉዳይ ግንኙነት ስለመፍጠር አለምፍጠሩ ለቀረባቸው ጥያቄ “ጋዜጦቹ የሚያወሩት እሱን ከሆነ እንግዲያውስ ጉዳዩ ያ ነው። እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ የሚችሉበት ሁኔታ አለ። እናም የተወሰኑ ሂደቶች ወደፊት ገፍተዋል።

“ይህም ክለቡ በተለመደው መንገድ የሚሰራበት ልማድ ነው። በእግርኳሱ ዓለም ሰዎች ስለተጫዋቾች የማውራታቻው ነገር የሚፈለግ ነው። ሁሉም ነገር የሚሆን የሚመስለውም እንደዚያ ነው።” ሲሉ ምላሽ ሰጥተው ነበር። ይህ ምላሻቸውም ለአትሌቲኮ ማድሪድ አቤቱታ መነሻ ሳይሆን እንደማይቀር ታምኗል።

በባርሳ ላይ የሚቀርባው የአቤቱታ ውሳኔ የተላለፈውም የአትሌቲኮ  የአክስዮን ባለድርዎች ሰኞ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነበር።

የስፔኑ ጋዜጣ ይህን ይበል እንጂ ከአትሌቲኮ ማድሪድም ሆነ ከባርሴሎና በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

ግሪዝማን ባለፈው ክረምት ከስፔኗ መዲና ሊለቅ ነው በሚል ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ተያይዞ ሲዘገብ ቢቆይም፣ ነገር ግን ክለቡ የዝውውር እገዳ የተጣለበት መሆኑን ተከትሎ በክለቡ ለመቆየት ውሳኔ ላይ ደርሷል።

የግብ አዳኙ በ2014 ወደአትሌቲዎቹ ከተዛወረ በኋላ በ177 ጨዋታዎች ላይ 90 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ራሱን ከአውሮፓ ቀደምት አጥቂዎች ማካከል አንዱ ማድረግ ችሏል።

Advertisements