ኦሊቪየ ዥሩ በጥር ወር አርሰናልን ሊለቅ እንደሚችል ወኪሉ ተናገረ

ኦሊቪየ ዥሩ ትክክለኛ የዝውውር ጥያቄ የሚቀርብለት ከሆነ አርሰናልን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊለቅ እንደሚችል ወኪሉ ሚካኤል ማኑሎ ተናግሯል።

ዥሩ በዚህ የውድድር ዘመን አርሰናል በታህሳስ ወር መጀመሪያ ከዌስት ሃም ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተሰላፊ ሆኖ ከመጫወቱ ውጪ በሊጉ የመጀመሪያ ተሰላፊናት ሚናን አላገኘም። እናም በቀጣዩ ክረምት ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ሲል ተጨማሪ የመሰለፍ ዕድል ማግኘት ይፈልጋል።

ይሁን እንጂ የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ፈረንሳዊው ተጫዋች ለአጥቂ ክፍላቸው በተቀያሪ ወንበር ላይ የሚገኝ ብቃት ያለው አማራጭ ስለሚሆናቸው ፈፅሞ የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም።

ቬንገር በዥሩ ላይ ስላላቸው አቋም የፈረንሳይ የእግርኳስ ድረገፅ ለሆነው መርካቶ የተናገራው ማኑሎ “ይህ ነገሮችን ሊያወሳስባቸው እና ሊያጣርሰቸው ይችላል። ይህ አይነቱ ነገር የኦሊቪየም ሆነ የእኔ ተፈጥሯዊ ባህሪ አይደለም።

[ከግራ ወደቀኝ] ዥሩና ወኪሉ ማኑሎ

“እናም አሁን በሚቀርብልን [የዝውውር] ጥያቄ መሰረት በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን የምንነጋገር ይሆናል። የተሻለ ስራ ለማግኘት ወሳኙ ነገር የሚቀርብልን ነገር ወይም በዚህ የፀደይ ወቅት አለመሆኑ ነው። 

“ፍላጎቶች ይኖራሉ። አጥቂ የሚፈልጉ ክለቦች በሙሉ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እኛም የግድ መጠንቀቅ አለብን። እናም ግልፅ የሚሆን ነገር የሚኖር ከመሰለም ከዚህ በፊት የተነጋገርነውን ነገር እንዲቀይሩ ለማሳመን ወደአርሰን ቨንገር የምንመለስ ይሆናል።” በማለት ገልፅዋል።

ማኑሉ ዥሩ ወደ ሊግ 1 ይመለሳል የሚባለውን ነገር ውድቅ አድርጎ፣ ከማርሴ ጥያቄ ቀርቦለታል መባሉንም አስተባብሏል።

“ኦሊቪየ ወደፈረንሳይ ለመመለስ ባቀደው ጊዜ ላይ የሃሳብ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ ወደፈረንሳይ አይመለስም። 

“ከማርሴይ የቀረበ ፈላጎትም አልነበረም። ማርሴ እኛን ለማግኘት ሙከራ ስለማድረጉም መረጃ የለኝም።” በማለት ወኪሉ ተናግሯል።

ዥሩ በአጠቃላይ ውድድሮች በዚህ የውድድር ዘመን ለመድፈኞቹ ተሰልፎ በተጫወተባቸው 24 ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ አራቱ የመጀማሪያ ተሰላፊነት ዕድል ባላገኘባቸው የፕሪሚየር ሊጉ ጫዋታዎች ላይ ያስቆጠራቸው ናቸው። 

Advertisements