የሪያል ቤቲስ አስገርሚ ያለመሸነፍ ጉዞ በማላጋ ተገታ

ሪያል ቤቲስ በስምንት ጨዋታዎች ላይ የነበረው ያለመሸነፍ ጉዞ ሰኞ ምሽት በወራጅ ቀጠና ላይ በሚገኘው ማለጋ በደረሰበት የ2ለ0 ሽንፈት ሊገታ ችሏል።

ሰርጂዮ ሊዮን እና ቪክቶር ካማራሳ በተቆጠሩ ግቦች የኩዊኬ ስቴንሱ ማላጋ ከወራጅ ቀጠና አደጋ ክልሉ በአንድ ነጥብ ከፍ ብሎ እንዲቀመጥ አስችሎታል። ሆኖም ማላጋ በጁዋኪን አማካኝነት ከመስመር ያለፈች ግብ ማስቆጠር ቢችልም በጨዋታው ዳኛ ግቧ ሳትፀድቅ ቀርታለች።

ቀድሞ በማላጋ ተጫዋች የነበረውና ለፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን የተጭወተው የ36 ዓመቱ ሰርጂዮ የመጀመሪያዋን ግብ ለማላጋ በ24ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።

ከጨዋታው አጋማሽ መጠናቀቅ በፊትም ለሎስ ቬርዲብላንኮዎቹ ሁለተኛ ልታደርጋቸው የምትችል ግብ በጁዋኪን ቢቆጠርም በዚህ የውድድር ዘመን በስፔን ላ ሊጋ በተደጋጋሚ የውዝግብ መነሻ በሆነው በቪዲዮ የታገዘ የዳኝነት እገዛ ተግባራዊ አለመሆን መስመሯን ያለፈችው ግብ ብትቆጠርም በጨዋታው ዳኛ ሳትፀድቅ ቀርታለች።

ካማራሳ ለባለሜዳው ክለብ ከአንቶኒዮ ባራጋን የተሻማለትን ኳስ በጭንቅላቱ ገጭቶ ባስቆጠራት ሁለተኛ ግብ የተገኘው ነጥብ በስምንት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ያልደረሰበትን ሪያል ቤቲስን በ8ኛ ደረጃ፣ ማላጋን ደግሞ ከላ ሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ በአንድ ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ ችላለች።

Advertisements