የሴሪ ኣው ዳኛ መድሎ በመፋፀም ክስ ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል

ጣሊያናዊው ዳኛ ፒየሮ ጂያኮሜሊ ከሁለት ሳምንታት በፊት ላዚዮ በቶሪኖ 3ለ1 እንዲረታ አድርገዋል በሚል ከባድ ያለ ውዝግብ መነሾ ሆነው ነበር። ይህ ብቻ ሳይበቃ ዳኛው አሁንም በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ በለጠፉት ምስል ተጨማሪ አወዛጋቢ ጉዳይ በመፍጠራቸው የጣሊያን አቃቤያን ህግ የጥርጣሬ አይን ውስጥ እንዲገቡ ሆነዋል።

ጂያኮሜሊ የላዚዮውን ሲሮ ኢሞቢሊን ከቀይ ካርድ ከሜዳ ከማሰናበታቸውም በላይ ላዚዮን ግልፅ የፍፁም ቅጣት ምት ነፍገዋል። ጨዋታውን ተከትሎም ዳኛው በሰማያዊዎቹ ላይ ደባ ፈፅመዋል በሚል በይፋ ከሳምንቱ የዳኝነት ሚናቸው ተቀንሰው ነበር።

እንደጣሊያኑ ሚዲያ አንሳ ዘገባ ከሆነ ዳግሞ ጂያኮሜሊ የላዚዮ ቀንዳኛ ተቀናቃኝ የሆነው የሮማ የረጅም ጊዜ አምበሉን ፍራንቼስኮ ቶቲን ፎቶን በማህባራዊ ገፃቸው ላይ በመለጠፋቸው ከስራቸው የመሰናበት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። እንደሚዲያው ተጨማሪ ዘገባ ከሆነም የጣሊያን እግርኳስ ማህበር በጂያንኮሜሊ የሜዳ ላይ እና የሜዳ ውጪ ባህሪያት ላይ ምርመራው ማድረግ ጀምሯል።

የጣሊያን የፌደራሉ አቃቤ ህግ ቢሮም ዳኛው ከስራ ከሚያሰብት ጥፋት በተጨማሪ የወንጀል ክስ ይመስረትባችው አይመስረትባቸው የሚለውን ለመወሰን ስብሰባ የሚያደርግ ይሆናል።

Advertisements