አያክስ ሶስት አሰልጣኞቹን ከኃላፊነታቸው አነሳ

የሆላንዱ ክለብ አያክስ አምስተርዳም የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ማርሴል ኬዘርን እና የቡድናን የስልጠና ኃላፊዎች ሄኔ ስፓይከርማን እና ዴኒስ ቤርጋምፕን ካላቸው የስራ ኃላፊነት ማንሳቱን በይፋ ገልፅዋል።

የአራት ጊዜያት የአውሮፓ ሻምፒዮኑ አያክስ ዋናውን የቡድን አሰልጣኝ ኪዜርን የቀድሞውን አሰልጣኝ ፒተር ቦዥ ምትክ አድርጎ በሁለት ዓመታትና ለተጨማሪ ዓመታት የማገልገል አማራጭ ያለው የውል ስምምነት ያስፈረመው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ነበር።

ይሁን እንጂ ክለቡ ዛሬ (ሃሙስ) በይፋ በገለፀው መሰረት ኪዛርን እና ረዳቶቻቸውን ስፓይከርማንን እና ቤርጋምፕን ከስራ ኃላፊነታቸው በማንሳት የኮንትራት ስምምነቱ ገና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አቋርጧል። 

አያክስ ለመጨረሻ ጊዜ የሆላንዱን ሊግ ኤርዲዚየ ማሸነፍ የቻለው በ2014 በፍራንክ ደ ቦር የአሰልጣኝነት ዘመን ከበር። ከዚያ በኋላም ከዩሮፓ ሊግ ውድድር ውጪ ከመሆነቸው በፊት በሁለት የሻሚዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ውድድሮች ላይም በፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ተሸንፈው ወጥተዋል።

የአምስተርዳሙ ክለብ በዚህ የውድድር ዘመን በባደረጓቸው 17 ጨዋታዎች በሆላንዱ ሊግ ከመሪው ፒኤስቪ ከአምስት ነጥቦች አንሰው በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። መሪውን ክለብ እና በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ኤዚ አልካማርን ያሸነፉበትን ጨዋታ ጨምሮ ያለፉት የመጨረሻ ሶስት ጨዋታዎቻቸውን ማሸነፍ ችለዋል። ነገር ግን ረቡዕ ዕለት የሆላንድ የጥሎ ማለፍ የዋንጫ ውድድር ከሆነው ኬኤንቪቢ በከር በኤፍሲ ትዌንቴ ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

የክለቡ ኃላፊ የሆነው ተቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ኤድዊን ቫንደርሳር የአሰልጣኞቹ ስንብት አስመልክቶ “መጥፎ የክረምት ጊዜ እና የተቃወሰ የውድድር ዘመን ጅማሮን አሳልፈናል። ከእግርኳሳዊ እይታ አንፃር ከአውሮፓ ውድድር ውጪ መሆን ዝቅተኛ ነጥብ ነው። 

“በተለይም [የእግርኳስ ዳይሬክተሩ] ማርክ ኦቨርማርስ እና እኔ ስለዋናው ቡድን ቀጣይ የሆነ ተለዋዋጭ ውጤት ለወራት በተከታታይ ስንነጋገርበት ነበር።

“በዚህ መንገድ ደግሞ አያክስ ያቀደውን ደረጃ ያሳካል የሚል በራስ መተማመን አይኖረንም። በዚህም ፀፀት ይሰማኛል። ከቦርዱ ጋር በመመካከር በጋራ እንደአስተዳደር ማርሴል፣ ዴኒስ እና ሄኔ ለክለቡ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና እናቀርባለን።” ሲል ገልፅዋል።

Advertisements