ሲቪያ አሰልጣኙን ኤድዋርዶ ቤሪዞን አሰናበተ

የስፔኑ ክለብ ሲቪያ የክለቡን መጥፎ የሚባል ወቅታዊ ውጤት ተከትሎ ከገጠመው የካንሰር ህመም ለመዳን ከአንድ ሳምንት በፊት የቀዶ ህክምና ያደረጉትን አርጄንቲናዊ አሰልጣኝ፣ ኤድዋርዶ ቤሪዞን ከአልጣኝነት ማናቸው አሰናብቷል።

ሲቪያ በሁሉም ውድድሮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለ ሲሆን፣ ረቡዕ ዕለት ደግሞ በሪያል ሶሴዳድ 3ለ1 በሆነ ውጤት ከመሸነፍ በላሊጋው በ29 ነጥቦች ከመሪው ባርሴሎና በ13 ነጥቦች ርቆ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የክለቡ የቦርድ ዳይሬክተሮች አርብ ከቀትር በኋላ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ አሰልጣኙ ኤድዋርዶ ቤሪዞ ባሳዩት ወቅታዊ መጥፎ አቋም ከክለቡ የአሰልጣኝነት ኃላፊነታቸው ማንሳታቸውን ማምሻውን ክለቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ገልፅዋል።

Advertisements