አርሰናል ከ ሊቨርፑል | የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከሊቨርፑል በአንድ ነጥብ ብቻ አንሶ በመቀመጥ በውድድር ዘመኑ የቀደመው ጨዋታ በአንፊልድ የደረሰበትን የ4ለ0 ሽንፈት በኢሚራትስ ስታዲየም የመበቀል ውጥን ይዞ ይህን ጨዋታ የሚያደረግ ይሆናል።

ሊቨርፑል ባለፈው ሳምንት ቦርንማውዝን 4ለ0 በሆነ ውጤት በመርታት በአዎንታዊ ስሜት ውስጥ ሆኖ ወደለንደን በመጓያዝ ይህን ጨዋታ የሚያደረግ ቢሆንም በአንፃሩ አርሰናል በሁሉም ውድድሮች በሶስት ጨዋታዎች ላይ መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል።

የጨዋታው ዳኛ

ማርቲን አትኪንሰን

ዕድሜ፡ 46

በዚህ የውድድር ዘመን፡ አጫወቱ፡12 ጨዋታ፣ ቢጫ ካርድ ፡ 38፣ ቀይ ካርድ፡ 2

የሁለቱ ክለቦች ያለፉ ጨዋታ ውጤቶች

የአርሰናል ያለፉት ስድስት ጨዋታ ውጤቶች

በፕሪሚየር ሊግ: ድል፣ድል፣ሽን፣አቻ፣አቻ፣ድል
በሁሉም ውድድሮች:ሽን፣ድል፣አቻ፣አቻ፣ድል፣ድል

የሊቨርፑል ያለፉት ስድስት ጨዋታ ውጤቶች

በፕሪሚየር ሊጉ: አቻ፣ድል፣ድል፣አቻ፣አቻ፣አቻ፣ድል

በሁሉም ውድድሮች:ድል፣ድል፣ድል፣አቻ፣አቻ፣ድል

የቡድን ዜናዎች

አርሰናል በዛሬው የአርብ ምሽት ጨዋታ በሊግ ዋንጫ ጨዋታ ላይ የቋንጃ ጉዳት የገጠመውን ፈረንሳዊውን የፊት ተጫዋች ኦሊቪየ ዥሩን ይዞ ወደሜዳ አይገባም።

አሮን ራምሴም በተመሳሳይ ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይካተት ቢሆንም፣ ተከላካዩ ሽኮድራን ሙስታፊ ግን ገጥሞት ከነበረው የታፋ ጉዳት አገግሞ በዚህ በምሽቱ ጨዋታ ላይ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ጃክ ዋሼር በሳምንቱ አጋማሽ በሊግ ዋንጫ ላይ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ በዚህ ጨዋታ ለተከታታይ ሶስተኛ ጨዋታ የመኃል ሜዳ ሚናውን ይወጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ክሎፕ ከቦርንማውዝ ጨዋታ በፊት ወደልምምድ የተመለሰው ዮል ማቲፕ ለዚህ ጨዋታ መሰለፍ አለመሰለፉን የሚያረጋግጡ ሲሆን፣ ዳንኤል ስተሪጅም በጉዳት ምክኒያት እንዳለፉት ሳምንታት ሁሉ በዚህ ጨዋታ ላይም ይሰለፋል ተብሎ አይጠበቅም።

አልቤርቶ ሞሬኖ በምሽቱ ጨዋታ ከማይሰለፉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ቢሆንም፣ ኤምሬ ቻን የነበረበትን ቅጣት ጨርሶ እንዲሁም አዳም ላላና የቋሚ ተሰላፊነቱን ቦታ በማግኘት የመሰለፍ እድል ሊኖራቸው ይችላል።

ግምታዊ አሰላለፎች

የአርሰናል ግምታዊ አሰላለፍ:ቼክ፣ ቤለሪን፣ ኮሺየልኒ፣ ሞንሪል፣ ማይትላንድ-ኒለስ፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ኢዎቢ፣ ኦዚል፣ ሳንቼዝ፣ ላካዜቴ 

የሊቨርፑል ግምታዊ አሰላለፍ:ሚኞሌ፣ ጎሜዝ፣ ሎቭረን፣ ክላቫን፣ ሮበርትሰን፣ ቻን፣ ሄንደርሰን፣ ኦክሴድ-ቻንበርሌን፣ ኮቲንሆ፣ ሳላህ፣ ፊርሚኖ 

የሁለቱ ክለቦች የእርስበእርስ ግንኙነት

  • የዛሬው ምሽት ጨዋታ በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረግ 224ኛ የነጥብ ጨዋታ ሲሆን ሊቨርፑል 86 ጊዜ አርሰናል ደግሞ 78 ጊዜ ያህል አሸናፊ መሆን ሲችሉ በተቀሩት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
  • ያካለፉት ታሪካዊ አጋጣሚዎችን ከተመለከትን ሊቨርፑል በአርሰናል ሜዳ ያለው የአሸናፊነት ታሪክ አነስተኛ ቢሆንም የክሎፑ ቡድን ግን ከአርሰናል ጋር ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አልደረሰበትም። ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሁለቱ በለንደን የተደረጉ ናቸው።
  • ባልፈው የውድድር ዘመን መክፈቻ በነበረው የኤመራትስ ስታዲየም ተመሳሳይ ጨዋታ ሊቨርፑል በኮቲንሆ፣ ላላና እና ማኔ ግቦች አርሰናል 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሎ ነበር።
Advertisements