ስንብት / ሲቪያ ኤድዋርዶ ቤሪዞን አሰናበተ

6.jpg

የአንዳሉሺያኑ ሲቪያ ከህክምና ከተመለሱ ከአንድ ሳምንት በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ ኤድዋርዶ ቤሪዞን ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን አሳወቀ፡፡

ክለቡ እሮብ በሪያል ሶሴዳድ 3-1 ከተሸነፈ በኋላ ላለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባለመቻሉ ደካማ አቋም ማሳየቱን ቀጥሏል፡፡በዚህም መሰረት የክለቡ ቦርድ አሰልጣኙን ከሀላፊነታቸው ማንሳቱን አሳውቋል፡፡

የቀድሞ የሪቨር ፕሌት ተከላካይ የነበሩት ቤሪዞን ሆርጌ ሳምፓኦሊን ተክተው ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ወደ ሲቪያ ካቀኑ በኋላ በቅርቡ ከህመማቸው ቀዶ ጥገና አድርገው ባለፈው አርብ ወደ ስራቸው ቢመለሱም ሌቫንቴን ማሸነፍ ከብዷቸው 0-0 መለያት ችለው ነበር፡፡እሮብ ደግሞ በሶሲዳድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡፡በዚሁ ወር በርናባው ላይ በሪያል ማድሪድ 5-0 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ቤሪዞን በመተካት የቀድሞ የባርሴሎና አሰልጣኝ የነበረው ልዊስ ኤነሪኬ አዲሱ አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

ሲቪያ በቻምፕየንስ ሊጉ ከጆሴ ሞሪንሆው ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በጥሎማለፍ ጨዋታ ላይ በቀጣይ የካቲት ወር ላይ እንደሚጫወት ይታወቃል፡፡

Advertisements