“የልጅ አይነት ነው”- ሲሉ ጆሴ ሞሪንሆ የአንዳንድ ተጫዋቾቻቸው ውሳኔን ወቀሱ

6.jpg

ማንቸስተር ዩናይትድ ትናንት ምሽት ወደ ኪንግ ፓወር ስታድየም አቅንቶ ያደረገውን ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃ ተቆጥሮበት በአቻ ውጤት ከተለያ በኋላ ጆሴ ሞሪንሆ አንዳንድ ተጫዋቾቻቸው በጨዋታው የነበራቸው ውሳኔዎች “የልጅ አይነት” ሲሉ ወርፈዋል፡፡

የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ የፈረንጆቹ ክሪስማስ በአል ሰሞን የዋንጫ አሸናፊው እንደተለየ ብዙዎቹ ሀሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡የፔፕ ጓርዲዮላው ማን ሲቲዎች በፍጹም አስደናቂ ብቃት ሩጫቸውን ሲቀጥሉ ሌሎች ተፎካካሪ ቡድኖች ግን ሲቲዎችን ተከትሎ ለመሄድ አቅም አላገኙም፡፡

3

ሲቲዎች ትናንት ምሽትም ቦርንማውዝን አስተግደው በቀላሉ አራት ጎል አስቆጥረው ተጨማሪ ሶስት ነጥብ ሲያስመዘግቡ ሁለተኛ ሆነው ሲከተሉ የነበሩት ማን ዩናይትዶች በሌሲስተር የመጨረሻ ደቂቃ ጎል ከኪንግፓወር ስታድየም አንገታቸውን ደፍተው መውጣት ችለዋል፡፡

ዩናይትዶች ጨዋታውን በቀላሉ ሊያሸንፉበት የሚችሉበት አጋጣሚ ከባለሜዳዎቹ በቀይካርድ አንድ ተጫዋች እንኳን ተቀንሶ ሊጠቀሙበት አለመቻላቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡የመጨረሻዎቹን 25 ደቂቃዎች ጨዋታውን ሲመሩበት ከነበረው የ 2-1 ውጤት ማስፋት የሚችሉበት አጋጣሚዎች ቢያገኙም ፍጹም ሊታመን በማይችል መልኩ ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡

2.jpg

በተለይ ማርሻል፣ሊንጋርድ እና ራሽፎርድ ያልተጠቀሙበት አጋጣሚዎች ቡድኑን ዋጋ አስከፍሎታል፡፡ሊንጋርድ ግብ ጠባቂውን ጭምር አልፎ(ምስሉን ይመልከቱ) ባዶ ጎል ማስቆጠል ያልቻለበት እንዲሁም በአንድ አጋጣሚ ራሽፎርድ ተቀይሮ ከገባ በኋላ ከግብ ጠባቂ ጋር ፈት ለፊት ተገናኝቶ ለማለፍ ሞክሮ ያልተጠቀመበት ኳስ እጅግ አስቆጪ ነበሩ፡፡

ራሽፎርድ በሌላ አጋጣሚ ለሉካኩ በቀላሉ አሾልኮ ጨዋታውን መግደል የሚችሉበትን አጋጣሚ ኳሱን ለማቀበል ያመነታበት መንገድም ሌላው ለትችት የዳረገው ክስተት ሆኗል፡፡በመጨረሻ ግን ባለሜዳዎቹ በተከላካያቸው ማጉይር አማካኝነት ያስቆጠሩት ጎል የቀዮቹን ሰይጣኖች ለዋንጫ ያላቸውን ተስፋ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ቸልሶበታል፡፡

4.jpg

ጆሴ ከጨዋታው በኋላ የአንዳንድ ተጫዋቾቻቸው የልጅ አይነት ውሳኔዎች “አስቂኝ” በማለት ዋጋ እንዳስከፈላቸው ተናግረዋል፡፡”ማሸነፍ ያልቻልነው በጨዋታው አስገራሚ ኳሶችን መጠቀም ባለመቻላችን ነው፡፡በሁለተኛው ግማሽ በተጨማሪ የመከላከል ስህተት ነበረብን፡፡በመጨረሻ ብስለት ስለጎደለን እና ስሞሊንግ በመጎዳቱ ማጉይር ተጨማሪ ሰው አድርገው አስቆጥረውብናል፡፡”

ጆሴ የአንዳንድ ተጫዋቾቻቸው ብስለት ማጣት ከሌላው ወጣት ተጫዋቻቸው ቶም ማክ ቶሚኒ መማር እንደሚገባቸው ጠቆም አድርገው አልፈዋል፡፡

“ወጣቱ ቶም ማክ ቶሚኒ አሁንም ብዙ መማር ያለበት ተጫዋች ነው፡፡ ባለፈው አመት ይጫወት የነበረው ከልጆች ጋር ነበር ነገርግን የልጅ አይነት ውሳኔ አይሳሳትም፡፡ሌሎች ተጫዋቾች ግን ለአመታት የልጅ አይነት ውሳኔዎች ይወስናሉ፡፡”ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል፡፡

 

Advertisements