ቅጣት/ የሳውዝአምፕተኑ አጥቂ ቻርሊ ኦስቲን የሶስት ጨዋታ እገዳ ተጥሎበታል

skysports-premier-league-football-charlie-austin-southampton_4190645

የሳውዝአምፕተኑ አጥቂ ስፍራ ተጫዋች ቻርሊ ኦስቲን ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የሶስት ጨዋታዎች ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

እንግሊዛዊው ቅጣቱ የተጣለበት የሀደርስፊልዱን ግብ ጠባቁ ጆናስ ሎስልን መርገጡን ተከትሎ ሲሆን በእለቱ ዳኛው ድርጊቱን አለመመልከታቸውን ተከትሎም የእግር ኳስ ማህበሩ በምስል እይታ ክስተቱን በመመልከት ቻርሊ ኦስቲን ላይ የሶስት ጨዋታዎች እገዳ ጥሏል፡፡

ኦስቲን በማህበሩ የተጣለበትን ቅጣት የተቀበለ ሲሆን ክለቡ ሳውዝአምፕተን በቀጣይ በሊጉ ከቶትንሀም ሆትስፐርስ ማንችስተር ዩናይትድ እና ክርስታል ፓላስ ጋር ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎችም ውጭ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በኤፍ ኤ ካፕ ሳውዝአምፕተን ፉልሀምን በሚገጥመበት ጨዋታም ቅጣቱን ጨርሶ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል፡፡

የ28 አመቱ ቻርሊ ኦስቲን ባለፉት 5 የሊግ ጨዋታዎች 5 ግቦችን ከመረብ ማገናኘት ችሏል፡፡

Advertisements