ጉዳት/ ኦሊቪየር ጅሩድ በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ለ6 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል

nintchdbpict0003740403683

የአርሰናሉ ፊት አውራሪ መድፈኞቹ በካራባኦ ካፕ ዌስትሀም ዩናይትድን 1-0 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ የደረሰበትን የጡንቻ ጉዳት ተከትሎ ከሜዳ ለ6 ሳምንታት እንደሚርቅ የፈረንሳዩ ታማኝ ሚዲያ ለኪፕ ዘግቧል፡፡  

አሰልጣኝ አርሰን ዌንገር ጉዳቱ የከፋ አይደለም በቅርብ ሳምንታት ወደ ሜዳ ይመለሳል ቢሉም የፈረንሳዩ የስፖርት ጋዜጣ ግን እመኑኝ ኦሊቪየር ጅሩድን ለስድስት ሳምንታት አትመለከቱትም ብሏል፡፡

በአርሰናል ቤት የአሌክሳንደር ላካዜትን መምጣት ተከትሎ ተቀዳሚ ቦታውን ማስከበር ያልቻለው ኦሊቪየድ ጅሩድ በጥር ወር ክለቡን ይለቃል ተብሎ በስፋት ቢነገርም ከጉዳቱ እሰከ የካቲት ወር አለማገገሙን ተከትሎም በአርሰናል ቤት የመቆየቱን ነገር እርግጥ አድርጎታል፡፡

በዲዲዮ ዴሻምፕ በሚመራው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ቁጥር አንድ ተመራጭ የሆነው የ31 አመቱ ኦሊቪየ ጅሩድ በ2018 በሩሲያ ለሚዘጋጀው የአለም ዋንጫ ላይ ቦታውን ለማስከበር   ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ሲሆን የጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳቱን ተከትሎ ግን አርሰናል በሁሉም ውድድሮች በሚያደርጓቸው 10 ጨዋታዎች ውጪ ሆኗል፡፡

Advertisements