ሀሪ ኬን አለን ሺረር ለ22 አመት ይዞት የነበረውን ሪከርድ ሰበረ

የቶተንሀሙ የአጥቂ ተሰላፊ የሆነው እንግሊዛዊው ሀሪ ኬን አለን ሺረር በአንድ የካሌንደር አመት ይዞት የነበረውን የፕሪምየርሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድ ሰበረ።

ኬን ባለፈው ቅዳሜ በርንሌ ላይ ሀትሪክ በመስራት በ 2017 በፕሪምየርሊጉ ያስቆጠራቸው የጎል መጠን 36 ማድረስ ችሏል።

ይህ ደግሞ አለን ሺረር በ 1995 ለብላክበርን ሲጫወት በአንድ የካለንደር አመት ካስቆጠረው የጎል መጠን ጋር እንዲስተካከል አድርጎት ነበር።

ስፐርሶች 2017 ከመጠናቀቁ በፊት ዛሬ ከሳውዝሀምፕተን ጋር ጨዋታ የነበራቸው ሲሆን በዚህ ጨዋታ ሀሪ ኬን ሪከርዱን ሊያሻሽል እንደሚችል ተጠብቆ ነበር።

እንግሊዛዊው አጥቂ እንደተጠበቀው ስፐርሶች ሳውዝሀምፕተንን 5-2 ሲያሸንፉ ሌላ ሀትሪክ በመስራት  የቻለ ሲሆን ይህም በ2017 ያስቆጠረው የጎል መጠን 39 በማድረስ አለን ሺረር ለ 22 አመት ይዞት የነበረውን ሪከርድ ሰብሯል።

አለን ሺረር በትዊተር ገፁ ላይ ኬን በ 2017 አስደናቂ አመት እንዳሳለፈ በመግለፅ ሪከርድ መስበሩም እንደሚገባው ተናግሯል።

በአንድ የካሌንደር አመት ከፍተኛ የፕሪምየርሊግ አስቆጣሪዎች

39 – ሀሪ ኬን(2017)

36 – አለን ሺረር(1995)

35 – ሮቢን ቫንፔርሲ(2011)

34 – ትየሪ ኦነሪ (2004) ናቸው።

ኬን በአጠቃላይ ጨዋታዎች ደግሞ 56 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ይህ ደግሞ ሊዮ ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2017 ካስቆጠሩት 54 እና 53 ጎሎች ሁሉ የተሻለ ሆኗል። 

Advertisements