በቦክሲንግ ደይ ጨዋታ ውጤታማ ክለቦች የትኞቹ ናቸው?

ቦክሲንግ ደይ በፈረንጆቹ የገና በዓል ማግስት ባለው ቀን፣ ታህሳስ 17 (እንደአውሮፓውያን የቀን ቀመር ዴሴምበር 26) የሚከበር በዓል ሲሆን፣ የበዓሉ መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም ሆኖ በአብዛኛዎቹ የቀድሞ የብሪታንያ ግዛቶች ላይም ጭምር በሰፊው የሚበከር በዓል ነው።

በዚሁ መሰረት የፈረንጆቹን የገና በዓል ማብቃት ተከትሎ ባለው ቀን ዛሬ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተለማዷዊ የቦክሲንግ ደይ ጨዋታዎች ይከናወናሉ። 

ዛሬ (ማክሰኞ)፣ ነገ እና ከነገበስቲያ በሚካሄዱት የዚህ የውድድር ዘመን የቦክሲንግ ደይ ጨዋታዎች የትኞቹ ክለቦች ጠንክረው ይመጣሉ? የትኞቹ ክለቦችስ በገና በዓል የዞረ ድምር ስሜት ውስት ሆነው ነጥብ ይጥሉ ይሆን? ምላሹን ከጨዋታዎቹ ማጠናቀቅ በኋላ የምናውቅ ይሆናል። 

ባለፉት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመኖች ግን ማንችስተር ዩናይትድ፣ አርሰናልና ሊቨርፑል በቦክሲንግ ደይ ጨዋታ ድል የማድረግ ተለምዷዊ ታሪኮች ያሏቸው ሲሆን፣ አንዳድን ዝቅተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው ክለቦችም በእዚህ የጨዋታ ቀን አስደናቂ ውጤቶችን የማስመዝገብ ታሪኮችም አሏቸው።

ቤቲንግኤክስፐርት (bettingexpert.com የተሰኛው ድረገፅ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አበይት ክለቦች የቦክሲንግ ደይ የቀደመ ታሪክ የውጤት ቁጥራዊ የጥናት ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የድህረ ገና በዓል ጨዋታዎች እንደሌስተር እና ኒውካሰል ላሉ ክለቦች የተመቹ አይደሉም።

ለመሆኑ በአዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስባለፈው የውድድር ዘመን ባሉት ጊዜያት አበይት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በቦክሲንግ ደይ ጨዋታዎች ላይ ምን ያህል አማካኝ ነጥቦችን አስመዝግበው ይሆን? መልሱን ከታች ይመልከቱ።

# ክለብ አማካኝ
ነጥብ
18 ዌስት ብሮም 0.45
17 ሌስተር 0.45
16 ቦርንማውዝ 0.50
15 ኒውካሰል 0.80
14 ሳውዛምፕተን 1.20
13 ዋትፎርድ 1.25
12 ክሪስታል ፓላስ 1.25
11 ኤቨርተን  1.29
10 በርንሌይ 1.33
9 ስዋንሲ 1.40
8 ዌስትሃም 1.59
7 ስቶክ ሲቲ 1.63
6 ቼልሲ 1.70
5 ማን ሲቲ 1.78
4 ቶተንሃም  1.90
3 ሊቨርፑል 1.95
2 አርሰናል 2.05
1 ማን ዩናይትድ 2.57
Advertisements