ጆዜ ሞሪንሆ ዩናይትድ እስካሁን ለዝውውር ያወጣው 286 ሚ.ፓ በቂ እንዳልሆነ ገለፁ

ጆዜ ሞሪንሆ ከማንችስተር ሲቲ አንፃር ማንችስተር ዩናይትድ ለዝውውር ወጪ ያደረገው ገንዘብ በቂ እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ማንችስተር ሲቲ ዛሬ (ረቡዕ) የሚገጥመውን ኒውካሰልን የሚያሸንፍ ከሆነ ዩናይትድ ማክሰኞ በኦልትራፎርድ ከበርንሌይ ጋር 2ለ2 በሆነ ውጤት በማጠናቀቁ ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ በ15 ነጥቦች ርቀቆ ዝቅ ብሎ ሊቀመጥ ይችላል።

በእንግዳው ቡድን 2ለ0 ይመራ የነበረው የሞሪንሆው ቡድን ጄሴ ሊንጋርድ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ በጭማሪ ሰዓት የስቆጠረውን ግብ ጨምሮ ሁለት ግቦችን ባያስቆጥር ኖሮ ከዚህም የከፋ ውጤት ሊየስመዘግብ ይችል ነበር።

እንዲህ ዓይነቱ የነጥብ ልዩነት ከዩናይትድ ክብር አንፃር ተቀባይነት ይኖረው እንደሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጆዜ ሞሪንሆ “ትልቅ ክለብ መሆን እና ትልቅ የእግርኳስ ቡድን መሆን መሆን ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

“እኛ [በአሁኑ ጊዜ] ከዓለም ምርጥ ቡድኖች መካከል አንዱ ያልሆነውን አንድ የእግርኳስ ቡድን ዳግም የመገንባት በሁለተኛው የሙከራ ዓመት ላይ እንገኛለን። ማንችስተር ሲቲ በአጥቂ ዋጋ የመስመር ተከላካይ ገዝቷል። ስለትልልቅ ክለቦች ስትናገር እየተናገርክ ያለኸው ስለክለቡ ታሪክ ይሆናል።” በማለት መልሰዋል።

ዩናይትድ ሞሪንሆ በአሰልጣኝነት ከተረከቡበት 2016 አንስቶ በድምሩ 286 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ስለማድረጉም የተጠየቁት ፓርቱጋላዊው አሰልጣኝ “እሺ። [ነገር ግን] በቂ አይደለም። የትልቅ ክለቦች ዋጋ ከሌሎች ክለቦች የተለየ ነው። 

“ትልቅ ታሪካዊ ክለቦች በገበያው ላይ የመቀጣታቸው ነገር የተለመድ ነው። ምክኒያቱ ደግሞ ታሪካቸው ነው።” ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል።

በጥር የዝውውር መስኮት ወቅት ትልቅ የዝውውር ወጪ ለማውጣት ዕቅድ ይኖራቸው እንደሆን ለቀረበላቸው ጥያቄም ሞሪንሆ ምላሽ ሳይሰጡ የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉን ለቀው ወጥተዋል።

Advertisements