ሊቨርፑል ከ ሌስተር ሲቲ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቅድመ ቅኝት 

የፈረንጆቹ አሮጌው አመት በሚጠናቀቅበት የመጨረሻው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የክሎፑን ሊቨርፑልን እና በስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የታች አምናውን ሻምፒዮን ሌስተር ሲቲን ቅዳሜ አመሻሹ ላይ በአንፊልድ ያገናኛል።

ውድድር፡ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 21፣ 2010 ዓ.ም
ሰዓት: ምሽት 12:00
ሜዳ: አንፊልድ (ሊቨርፑል)

ሊቨርፑል በአጥቂ ክፍሉ ጠንካራ ብቃት ታግዞ ማክሰኞ ምሽት ስዋንሲ ሲቲን በአንፊልድ 5ለ0 በመርታት አስደናቂ ጉዞውን ማሳየቱን ቀጥሎበታል። በዚህ ሌስተር ሲቲን በሚገጥምበት የፈረንጆቹ ዓመት የመጨረሻ ጨዋታውም እያሳየ የሚገኘውን ጠንካራ ብቃት ለማስቀጠል ይጫወታል።

ቀበሮዎቹ በክላውድ ፑየል ጥሩ ጅማሮ ማሳየት ቢችሉም፣ በዚህ ወር መጀመሪያ በኪንግ ፓወር ስታዲየም በክሪስታል ፓላስ ከደረሰባቸው የ3ለ0 ሽንፈት በኋላ መልካም ጉዟቸው እክል ገጥሞታል። ባለፈው ሳምንት በኪንግ ፓወር ስታዲየም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የአጥቂ ክፍላቸው ጥሩ የሚባል ነገር ማሳየት ቢችልም በሳምንቱ አጋማሽ ከዋትፎርድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ግን ያን ብቃት መድገም ሳይቻላቸው ቀርተዋል።

የፑየሉ ቡድን በቪካሬጅ ሮድ ባደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በሪያድ ማህሬዝ የጨዋታውን የመጀመሪያዋ ግብ በማስቆጠር መልካም ጅማሮ የነበረው ቢሆንም የግብ ክልሉን በሚገባ መጠበቅ ባለመቻሉ ግን የኋላ ኋላ የ2ለ1 ሽንፈት ደርሶበታል።

የርገን ክሎፕ መላውን የውድድር ዘመን የተከላካይ ክፍላቸው ትልቅ የክለቡ ችግር ሆኖ ቆይቷል። ነገር ግን ማክሰኞ ምሽት ስዋንሲን 5ለ0 በረታበት ጨዋታ መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል። ፊሊፔ ኮቲንሆ በማጥቃት ክልል ውስጥ ጠንካራ የሚባል ብቃት ባማሳየት፣ ሮቤርቶ ፊርሚኖ (ሁለት ግብ በማስቆጠር)፣ እና መሐመድ ሳላህ (ሁለት የግብ ዕድል በማመቻቸት) ክለቡ በደጋፊው ፊት ድልን እንዲቀዳጅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

የክለቦቹ ያለፉት አምስት ጨዋታ ውጤቶች


ሊቨርፑል

5-0 ድል በሜዳው ከከስዋንሲ ጋር
3-3 አቻ በአርሰናል ሜዳ 
0-4 ድል በቦርንማውዝ ሜዳ
0-0 አቻ በሜዳው ከዌስትብሮም ጋር
1-1 አቻ በሜዳው ከ ኤቨርተን ጋር

ሌስተር
2-1 ሽንፈት በዋትፎርድ ሜዳ
2-2 አቻ በሜዳው ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር
1-1 ሽንፈት በሲቲ ሜዳው በመለያ ምት (በሊግ ዋንጫ)
0-3 ሽንፈት በሜዳው በክሪስታል ፓላስ
1-4 ድል በሳውዛምፕተን ሜዳ

የሊቨርፑል እና ሌስተር የከዚህ በፊት ግንኙነቶች

  • በመስከረም አጋማሽ ወር በኪንግፓወር ባደረጉት ጨዋታ ሊቨርፑል ከኋላ ተነስቶ 3ለ2 በማሸነፍ በጨዋታ ላይ አምስት ግቦች ተቆጥረዋል።
  • ሁለቱ ክለቦች ባደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በአራቱ ላይ ግቦች ተቆጥረዋል።
  • ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም በአንፊልድ ካደረጓቸው 44 ጨዋታዎች ሊቨርፑል 23 ሲያሸንፍ ሌስተድ ደግሞ 11 ጨዋታዎች ላይ አሸናፊ ሆኗል።

ግምታዊ የመጀመሪያ 11ተሰላፊዎች

ሊቨርፑል
አሰላለፍ: 4-3-3
ግምታዊ 11 ተሰላፊዎች
ግብጠባቂ:ሚኞሌ
ተከላካዮች:ጎሜዝ፣ ማቲፕ፣ ሎቭረን፣ ሮበርትሰን
አማካኞች: ቻን፣ ዋይናልደም፣ ኮቲንሆ
አጥቂዎች:ሳላህ፣ ማኔ፣ ፊርሚኖ

ሌስተር ሲቲ
ግምታዊ አሰላለፍ: 4-2-3-1
ግምታዊ የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች
ግብጠባቂ:ሹማይክል
ተከላካዮች:ድራጎቪች፣ ሞርጋን፣ ማጉዋየር፣ ፉክስ፣ 
የተከላካይ አማካኞች:ንዲዲ፣ ኢቦራ
የተከላካይ አማካኞች:ማህሬዝ፣ ግሬይ፣ ቺልዌል
አጥቂ:ቫርዲ

Advertisements