ዝላታን ኢብራሂሞቪች በጉዳት ምክኒያት ለአንድ ወር ከሜዳ ይርቃል

የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በገጠመው የጉልበት ጉዳት ለእንድ ወር ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኙ ሆዜ ሞሪንሆ ተናግረዋል።

የቀድሞው የስዊዲን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ የሞሪንሆው ቡድን ቅዳሜ ምሽት ከሳውዛምፕተን ጋር 0ለ0 በሆነ ውጤት ባጠናቀቀበት ጨዋታ ላይ መሰለፍ ከቻሉት ተጫዋቾች ውስጥ አልተካተተም።

ኢብራሂሞቪች ያለፈው የውድድር ዘመን ሲጠናቀቀ ዩናይትድን ከመልቀቅ ይልቅ በክለቡ ዳግመኛ ለመቆየት የኮንታርት ፊርማውን ያኖረው ባለፈው ክረምት ነበር። ነገር ግን ገጥሞት በነበረው ከባድ የጉልበት ጉዳት በአዲሱ የውድድር ዘመን እስከህዳር ወር ድረስ ወደጨዋታ መመለስ አልቻለም።

ይሁን እንጂ ከሳውዛምተን ጋር ባደረጉት የቅዳሜው ጨዋታ ሉካኩ በገጠማው ጉዳት በቃሬዛ ከሜዳ ሲወጣ የተመለከቱት ሞሪንሆ ኢብራሂሞቪችም ዳግመኛ ጉደት የገጠመው መሆኑን ተናግረዋል።

“ኢብራሂሞቪችን ለወራት አጥተነዋል። ለማገገም የሚያደረገው እንቅስቃሴም ተገቷል። መጫወት የሚያስችለውን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ለበርካታ ወራት ይህን ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ነበር።” ሲሉ ሞሪንሆ ተናግረዋል።

Advertisements