የሄሱስ እና የዴብሩይን ጉዳት ሲቲዎች አሌክሲስ ሳንቼዝን እንዲያዘዋውሩ ያስገድዳቸው ይሆን?

ማን ሲቲዎች ወደ ሴልሁርስት ፓርክ አቅንተው ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያለጎል በተለያዩበት ጨዋታ ላይ ሁለት ተጫዋቾች ተጎድቶባቸዋል።የነዚህ ተጫዋቾች ጉዳት ፔፕ ጓርዲዮላን አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማዘዋወር ያስገድደው ይሆን?ጓርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ በሳንቼዝ ዝውውር ዙሪያ ሀሳቡን ሰጥቷል።

በመጨረሻም ማን ሲቲዎች በፕሪምየርሊጉ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሲያደርጉት የነበረው ሩጫ ባልታሰበው ክሪስታል ፓላሶች ተቋጭቷል።ለመጀመሪያ ጊዜም ጎል ሳያስቆጥሩ መውጣት ችለዋል።

ባለሜዳዎቹ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ቢችሉ ኖሮ ሲቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈትን ለመጎንጨት ይቃረቡ ነበር።

ነገርግን የፍፁም ቅጣት ምቱ በመሳቱ ጨዋታው በአቻነት ለመጠናቀቅ ችሏል።

እንግዳ ዎቹ በጨዋታው ነጥብ ከመጣላቸው በተጨማሪ ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸው በጉዳት አጥተዋል።

ብራዚላዊው ሄሱስ  በጉልበት ጉዳት ሜዳውን እያለቀሰ ሲለቅ ሌላው የጉዳት ሰለባ የሆነው ኬቨን ዴብሩይን በቃሬዛ ሊወጣ ችሏል።

የሁለቱ ተጫዋቾች ጉዳት ጠንከር ያለ የሚመስል በመሆኑ በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ላይ ወደ ሜዳ የመመለስ እድል አይኖራቸውም።

ከጨዋታው በኋላ ስለ ተጫዋቹ ጉዳት የተናገረው ፔፕ ጓርዲዮላ ሄሱስ ለአንድ ወይም ለሁለት ወር ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ሲናገር በዴብሩይን ጉዳት ዙሪያ ግን ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ የሀኪሞች የምርመራ ውጤት እንደሚጠብቅ ተናግሯል።

ነገርግን በሁለቱ ተጫዋቾች ጉዳት ምክንያት ፔፕ ጓርዲዮላ አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማዘዋወር እንደሚያስገድደው በማመን ብዙ የአርሰናል ደጋፊዎች ስጋት አድሮባቸዋል።

ከወዲሁም ሳንቼዝ ከአርሰናል መልቀቁ እንደማይቀር በመረዳት አንዳንድ የመድፈኞቹ ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ስንብታቸውን ለሳንቼዝ እያቀረቡለት ይገኛሉ።[የአንዳንድ ደጋፊዎች አስተያየት ቀጥሎ ይመልከቱ]

ሳንቼዝ ከአርሰናል ጋር እስካሁን ውሉን ባለማራዘሙ እንዲሁም ኮንትራቱን በሰኔ ወር ላይ ስለሚጨርስ መድፈኞቹ በነፃ ላለማጣት ነገ በሚከፈተው የጥር የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን የመሸጥ እድላቸው የሰፋ ነው።

ሲቲዎች ደግሞ ባለፈው የክረምት የዝውውር መስኮት ላይ የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ለማዘዋወር ተቃርበው አርሰናሎች ተተኪ ባለማግኘታቸው ዝውውሩን መሰናከሉ ይታወሳል።

ሲቲዎች ዛሬ ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸው ላይ ጠንከር ያለ ጉዳት በመድረሱ ፊታቸውን በድጋሚ ወደ ሳንቼዝ ማድረጋቸው እንደማይቀር እየተነገረ ይገኛል።

በሳንቼዝ ጉዳይ ላይ ከጨዋታው በኋላ ጥያቄ የቀረበለት ፔፕ “እሱ የአርሰናል ተጫዋች ነው ከክለቡ ጋርም እንደሚቆይ አስባለው።አሁን ከዛሬው ጨዋታ የምናገግምበት ጊዜ ነው፣አንዳንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቃላችሁ ነገርግን በጭንቅላቴ ብዙ የማስባቸው ነገሮች አሉ።

“በሁለት ቀናት ውስጥ ሌላ ጨዋታ አለብን።ስለ ዝውውሩ እና ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ስብሰባ አድርገን የተሻለውን ነገር እንወስናለን።”።ሲሉ ተናግረዋል።

Advertisements