ኤቨርተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቅድመ ቅኝት

በፈርንጆቹ አዲስ ዓመት በዓል ቀን በሚደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቢግ ሳምን ከቀጠረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን ኤቨርተን እና በሶስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ላይ  በአቻ ውጤት ያጠናቀቀውን የሆዜ ሞሪንሆውን ማንችስተር ዩናይትድን በጉዲሰን ፓርክ ዛሬ (ሰኞ) ምሽት ያገናኛል።

ጨዋታ፡ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ቀን፡ ሰኞ ታህሳስ 23 (በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት) 
ሰዓት፡ 2፡30
ሜዳ፡ ጉዲሰን ፓርክ (ሊቨርፑል)

የቡድኖች ወቅታዊ ዜናዎች

ኤቨርተን
ኤቨርተን በጉዳት ላይ የቆዩትን ጄምስ ማካርቲን እና ያኒክ ቦላሲን የመጀመሪያ ተሰላፊ ለማድረግ ከጨዋታው በፊት የአቋም ፍተሻ የሚያደርግ ይሆናል።

ኢድሪስ ጉዬ ገጥሞት ከነበረው የቋንጃ ጉዳት አገግሞ በዚህ ጨዋታ ላይ እንደሚሰለፍ ሲጠበቅ፣ ሌይተን ቤንስ እና ሮዝ ባርክሌይ ግን አሁንም በጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ማንችስተር ዩናይትድ
ማንችስተር ዩናይትድ በጉዳት ምክኒያት ያለአጥቂው ሮሜሉ ሉካኩ እና ዝላታን ኢብራሂሞቪች ወደመርሲሳይድ የሚያቀና ይሆናል።

አሽሊ ያንግ በሶስት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት፣ እንዲሁም አምበሉ ማይክል ካሪክ፣ ኤሪክ ቤሊ፣ ክሪስ ስሞሊምግ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሺያ እና ማቲዮ ዳርሜን በጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

ስለጨዋታው ምን ተባለ?
የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ: “ልጆቹ ደካማውን ቡድን ለመቀየር ፍፁም ልዩ የሆነ ነገር አድርገዋል። በዘጠኝ ጨዋታ የተቆጠረብን አራት ግብ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በወራጅ ቀጠናው አደጋ ውጪ ሆነን እንድንተርፍ ያደርገናል።…ነገር ግን ይህንን ንገር ወደፊትም  ማስቀጠል ይኖርብናል።

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካኝ ፖል ፖግባ፡ “[ከሳውዛምፕተን ጋር ባደረግነው ጨዋታ] አልተሸነፍንም። ነገር ግን መንቃት እና ዳግም ወደድል መመለስ አለብን። አሁንም አቻ ውጥተናል። ማሸነፍ የሚገባንን ሶስት ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቀናል። የሆነ መቀየር ያለበት ነገር አለ። ወደማሸነፍም መለወጥ አለብን።

“በመጀመሪያው ቀን [በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት] ከኤቨርተን ጋር እንጫወታለን እግርኳስ እንዲህ ነው። ነገ ሌላ ቀን ነው። ስለዚህ ወደዚያ አምርተን ማሸነፍ አለብን።

ግምታዊ አሰለላለፍ

የኤቨርተን ግምታዊ 11 ተሰላፊዎች: ፒክፎርድ፣ ኬኒ፣ ዊሊያምስ፣ ጃጊየልካ፣ ማርቲና፣ ሌነን፣ ጉዬ፣ ሽናይደርሊን፣ ሲጉርድሰን፣ ሩኒ፣ ካልቨርት ሌቪን

የማንችስተር ዩናይትድ ግምታዊ 11 ተሰላፊዎች: ደ ኽያ፣ ቫሌንሺያ፣ ጆንስ፣ ስሞሊንግ፣ ሻው፣ ፖግባ፣ ማቲች፣ ሊንጋርድ፣ ማርሻል፣ ማታ፣ ራሽፎርድ

የኦፕታ የሁለቱ ክለቦች ቁጥራዊ መረጃዎች

  • ኤቨርተን ከ2010 አንስቶ ከማን ዩናይትድ ጋር በሜዳው ካደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች በአራቱ አሸናፊ ሆነዋል (አቻ2 ሽንፈት2)።
  • ማንችስተር ዩናይትድ ይህን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ በአንድ ቡድን ላይ በርካታ የፕሪሚየር ዲል በመቀዳጀት (34)  አስቶንቪላን ማሸነፍ ከቻሉትው ጋር የሚስተካከል የድል ቁጥር ክብረወሰን ይይዛል።
  • ማንችስተር ዩናይትድ በሁሉም ውድድሮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ኤቨርተንን ድል ማድረግ የቻለባቸውን ሰባት ግቦች ማስቆጠር የቻለው 10 ደቂቃ በቀረው የጨዋታ ጊዜ ውስጥ ነው።
  • ማንችስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች ላይ መረቡን ሳያስጠብቅ ወጥቷል። 
  • ሳም አላርዳይስ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለቱን ካሸነፉ በኋላ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ካደረጓቸው 21 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በአንዱ ብቻ ነው (አቻ 5፣ ሽንፈት15)።
  • ጆዜ ሞሪንሆ ከሳም አላርዳይስ ጋር ባደረጓቸው 11 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በየትኛውም ላይ ሽንፈት አልገጠማቸውም (ድል8 አቻ3)። 
  • ዋይኒ ሩኒ በፕሪሚየር ሊጉ በተለያዩ 36 ክለቦች ላይ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፣ በዚህም የሚበልጡት ፍራንክ ላምፓርድ (39)፣ አንዲ ኮል (38) እና አላን ሺረር (37) ብቻ ናቸው። 
  • ሩኒ ከገጠማቸው የሊጉ ክለቦች ሁሉ ብዙ ጊዜ ግብ ሳየስቆጥር የወጣው ማንችስተር ዩናይትድን በገጠመባቸው (5) ጨዋታዎች ነው።
  • ሩኒ ለመጨረሻ ጊዜ ከበላይ ስድስት ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ በተቆጠሩ ስምንት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበረው (ስድስት አገባ፣ ሁለት አመቻቸ)
Advertisements