ኹዋን ማታ በእንግሊዙ ጋዜጣ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ተሸላሚ ሆነ

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካኝ ኹዋን ማታ በእንግሊዙ ዕለታዊ ጋዜጣ፣ ዘ ጋርዲያን ልዩ በሆነ ስፓርታዊ ቸርነት ሌሎችን በመርዳት የስፖርቱ ዓለም ተምሳሌት በመሆኑ የ2017 የዘ ጋርዲያን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በሚል ሽልማት ተበርክቶለታል።

ዘ ጋርዲያን ይህን ሽልማት የጀመርው በ2016 ሲሆን የመጀመሪያው ተሸላሚም ጣሊያናዊው የካግሊያሪ ተከላካይ ፋቢዮ ፒስካኔ ነበር።

ስፔናዊው አማካኝ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ከሚያሳዩት ብቃት በተጨማሪ የእግርኳስ ተጫዋቾች ከሚያገኙት ደምወዝ “ስስትን ብቻ መገንባት ብቻ ሳይሆን በእግርኳሱ ላይ ያላቸውን ኃይልና ኃብት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መደበኛ ሰዎችን ለመርዳት” ማዋል እንደሚችሉም ማሳየቱን ጋዜጣው ገልፅዋል።

ማታ ከአምስት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ17 ሃገራት ከተወጣጡ ከሌሎች 35 የእግርኳሱ ዓለም ሰዎች ጋር በመሆን “የጋራ ግብ” ላሉት ዓላማ የደመወዛቸውን 1 በመቶ ገቢ ለእግርኳስ የግብረሰናይ ተቋማት አበርክቷል።

የሪያል ማድሪድ የታዳጊዎች የስልጠና ማዕከል ፍሬ የሆነው የ29 ዓመቱ የቀድሞ የቫሌንሺያና የቼልሲ ተጫዋች ኹዋን ማታ ማንችስተር ዩናይትድን በ37 ሚ.ፓ ከተቀላቀለበት 2014 አንስቶ በሁሉም ውድድሮች ላይ 127 ጨዋታዎችን አድርጎ 40 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጉዳት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የቋሚ ተሰላፊነት ሚናን ማግኘት አልቻለም ነበር።

Advertisements