በውድድር አመቱ መጨረሻ ኮንትራታቸውን የሚያጠናቅቁ የፕሪምየርሊጉ ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

የጥር የዝውውር መስኮት በፈረንጆቹ ከጥር አንድ ጀምሮ መከፈቱን ተከትሎ የአውሮፓ ቡድኖች በዝውውሩ ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።ቀጣዩ መረጃም በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በውድድር አመቱ መጨረሻ ኮንትራታቸው የሚጠናቀቅ ተጫዋቾች ምናልባትም በተከፈተው የዝውውር መስኮት ወደ ሌላ ክለብ ሊያመሩ የሚችሉ ተጫዋቾችን ይነግረናል

የመድፈኞቹ ኮከብ አሌክሲስ ሳንቼዝ ኮንትራታቸው በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሚያጠናቅቁት ተጫዋቾች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ሆኗል።

ተጫዋቹ እስካሁን ድረስ ከአርሰናል ጋር ኮንትራቱን ባለማራዘሙ ከክለቡ ጋር የመለያየት እድሉ እየሰፋ መጥቷል።

ሌላው የቡድን አጋሩ የሆነው ጀርመናዊው ሜሱት ኦዚልም እንዲሁ ከመድፈኞቹ ጋር የመውጫ በር ላይ ተቆመ ሌላኛው ተጫዋች ነው።ጃክ ዊልሼር እና ጄንኪንሰንም ኮንትራታቸው ሊጠናቀቅ ስድስት ወራት ብቻ ቀርቷቸዋል።

 ዩናይትዶችም እንዲሁ የአንዳንድ ተጫዋቾቻቸው ኮንትራታቸው በውድድር አመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።ፌሌይኒ እና ካሪክ ከቡድኑ ጋር ይቆያሉ ተብሎ ስለማይገመት በነፃ ዝውውር እንደሚለቁ ይጠበቃል።

የሄሬራ፣ሾው፣ማታ፣ብሊንድ እና የያንግ ኮንትራታቸው የሚጠናቀቅ ቢሆንም ለተጨማሪ 12 ወራት እንደሚያራዝሙ የሚጠበቅ በመሆኑ በቀጣዩ የውድድር አመትም ከቡድኑ ጋር እንደሚቆዩ ይጠበቃል።

ከታች በዝርዝር በውድድር አመቱ ኮንትራታቸው የሚያጠናቅቁ ተጫዋቾች ቀርቧል።

አርሰናል

ፐር መርትሳከር (በጡረታ)

ሳንቲ ካዞርላ

ሜሱት ኦዚል

ካርል ጄንኪንሰን

ጃክ ዊልሼር

አሌክሲስ ሳንቼዝ

ቦርንማውዝ

አርተር ቦሩች

ሮይስ ዊጊንስ

ማርክ ፑ

ብራይተን

ኒኪ ማኤንፓ

ኡው ሁኒሚር

ስቲቭ ሲድዌል

ሊያም ሮሲኒየር

ቲም ክሩል

ጋኤታን ቦንግ

ብሩኖ

ካዜንጋ ሉዋልዋ

በርንሌ

ዲን ማርኔ

አንደርስ ሊንዲጋርድ

ስቴፈን ዋርድ

ፍሬድሪክ ኡልቬስታድ

ስኮት አርፊልድ

ቼልሲ

ዊሊ ካባሌሮ

ኤድዋርዶ

ማቲች ዲላች

ክሪስታል ፓላስ

ጁሊያን ስፒሮኒ

ዳሚየን ዴላኒ

ዮሀን ካባይ

ጀምስ ማክአርተር

ዋይን ሄንሲ

ባካሪ ሳኮ

ጆኤል ዋርድ

ማርቲን ኬሊ

ቹንግ ዮንግ ሊ

ፍሪዲ ላዳፖ

ኤቨርተን

ጆኤል ሮብልስ

ሮስ ባርክሌይ

አሮን ሌነን

ኸደርስፊልድ

ሮበርት ግሪን

ዲን ኋይትሄድ

ማርቲን ክራኒ

ጆናስ ሎስል

ፍሎረንት ሀደርጎናጅ

ካሰይ ፓልመር

ሌሲስተር

ቤን ሀመር

ሮበርት ሁዝ 

አሌክሳንደር ድራኮቪች

ሊቨርፑል

ኤምሬ ቻን

ማን ሲቲ

ፈርናንዲንሆ

ያያ ቱሬ

ማን ዩናይትድ

ዝላታን ኢብራሂሞቪች

ማይክል ካሪክ

ዳሊ ብሊንድ (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ማርዋን ፌሌይኒ

አሽሊ ያንግ (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ሁዋን ማታ (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ሉክ ሻው (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

አንደር ሄሬራ (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ኒውካስትል


ጄሱስ ጎሜዝ

ፖል ዱሜት

ማሳዲዮ ሀይዳራ

ኩርቲስ ጉድ

ሳውዝሀምፕተን

ስርዋርት ቴይለር

ጃክ ሮስ

ፍሎሪን ጋርዶስ

ጀርሜ  ፒድ

ስቶክ ሲቲ

ግሌን ጆንሰን

ቻርሊ አዳም

ጄሲ

ጃኮብ ሀውጋርድ

ስዋንሲ

ሊዮን ብሪተን (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ካይል ባርትሌ

አንግል ራንግል

ሱንግ-ዮንግ ኪ

ሬናቶ ሳንቼዝ

ኦሊቨር ማክብሩኔ

ኬንጂ ጎሬ

ቶተንሀም

ሚሼል ቮርም

ዋትፎርድ

ቤን ዋትሰን

ኦሬስቲስ ካርኔዚስ

ሚግዌል ብሪቶስ

ጆሴ ሆሊባስ

ሞላ ዋጉ

አንድሬ ከሪሎ

ዌስትብሮም

ጋሪዝ ባሪ

ቦአዝ ማሂል

ጀምስ ሞሪሰን (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ክሪስ ብረንት (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ጋሪዝ ማክ አውሪል

ግሪዝጎርዝክ ክሪቾውያክ

ክላውዲዮ ያኮብ (ክለቡ ኮንትራቱን የማራዘም አማራጭ አለው)

ዌስትሀም


ጀምስ ኮሚንስ

ዲያፍራ ሳኮ

እነዚህ ክለቦች ኮንትራታቸው በውድድሩ አመቱ መጨረሻ የሚያጠናቀቁ ተጫዋቾቻቸውን ኮንትራታቸውን ማራዘም ካልቻሉ ወይም በተከፈተው የጥር የዝውውር መስኮት ለሌላ ክለብ መሸጥ ካልቻሉ ተጫዋቾቻቸው በክረምቱ የዝውውር መስከለት ክለባቸውን በነፃ የሚለቁ ይሆናል። 

Advertisements