የዕለተ ማክሰኞ አበይት የዝውውር ወሬዎች

የአውሮፓ የጥር ወር የዝውውር መስኮት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ትናንት [ሰኞ] በይፋ ተከፍቷል። ኢትዮአዲስስፖርትም ለአንድ ወራት ያህል የሚዘልቀውን ትኩስ የዝውውር ወሬዎችን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአጭር በአጭሩ ወደእናንተ ማድረሷን እነሆ ጀምራለች።

ክሩዝ ለማንችስተር ዩናይትድ ሊሸጥ ነው


እንደእንግሊዙ ጋዜጣ ኤክስፕሬስ መረጃ ከሆነ ሪያል ማድሪድ የፒኤስጂውን ኮከብ ኔይማርን ለማዛወር የገንዘብ አቅሙን ከፍ ለማድረግ ቶኒ ክሩዝን ለማንችስተር ለመሸጥ ተዘጋጅቷል።

ማድሪድ ኔይማርን የሮናልዶ ምትክ አድርጎ ወደክለቡ የማምጣት የረጅም ጊዜ ፍላጎት አለው። ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ሳይሆን ፒኤስጂም የክሩዝ ፈላጊ ነው።  


ባርሳ ለኮቲንሆ 180 ሚ.ዩ. መክፈል ይጠበቅበታል


ሊቨርፑል የባርሴሎና የዝውውር ዒላማ ለሆነው ፊሊፔ ኮቲንሆ 180 ሚ.ዩ. ዋጋ ያወጣለት መሆኑን የስፔኑ ኦንዳ ሴና ሬድዮ ዘገባ አመልክቷል።

ብራዚላዊው ተጫዋች ከካታላኑ ክለብ ጋር ስሙ ለረጅም ጊዜያት በዝውውር ጉዳይ ተያይዞ የቆየ ሲሆን፣ የየርገን ክሎፑ ቡድን ለኮከቡ ተጫዋቹ የሚፈልጉትን ያህል ክፍያ ማግኘት የሚችሉ ከሆነ ተጫዋቹን ለመሸጥ ፈቃደኛ ናቸው።


ቼልሲ ቪዳልን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀመረ


ቼልሲ የባየር ሙኒኩን አማካኝ አርቱሮ ቪዳልን በጥር የዝውውር መስኮት ማዛወር በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር ከተጫዋቹ ጋር ግንኙነት ማድረግ መጀመሩን የጀርመኑ ጋዜጣ ቢልድ ዘግቧል።

ሰማያዊዎቹ ከዚህ ቀደም ለተወሰኑ ጊዜያት ስማቸው ከቺሊያዊው ተጫዋች ጋር በዝውውር ጉዳይ ተያይዞ የቆየ ሲሆን፣ አሁንም ትልቅ የዋጋ ስምምነት ይዘው ወደገበያው ብቅ ብለዋል።

ቪዳል ከባየር ሙኒክ ጋር እ.ኤ.አ. እስከ2019 ድረስ የሚያቆየው የኮንታራት ስምምነት ያለው ቢሆንም ተጫዋቹ መልቀቅ የሚፈልግ ከሆነ እና ጥሩ የዝውውር ስምምነት የሚቀርብ ከሆነ ሊሸጥ ይችላል።


ማን ዩናይትድ አንድሬ ጎሜዝን ለማዛወር ተዘጋጅቷል


የጣሊያን የስፖርት ድረገፅ የሆነው ኢል ቢያንኮኔሮ እንደዘገበው ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድ የባርሴሎናውን አማካኝ አንድሬ ጎሜዝን ለማስፈረም ጥረት ለማድረግ ተዘጋጅቷል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ ቀደም ሲል ለፓርቱጋላዊው ተጫዋች 35 ሚ.ፓ. አስቀድመው አቅርበው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ፉክክሩን ባለመቻለቸው እጅ ሰጥተው ነበር። 


መሲ፣ ዴሌ አሊ በባርሳ እንዲጫወት ፍላጎት አለው


ሊዮኔል መሲ ባርሴሎና ለቶተንሃሙ አማካኝ ዴሌ አሊ ዝውውር ዋጋ እንዲያቀርብ ፍላጎት ያለው መሆኑን የዘገበው የጣሊያኑ ጋዜጣ ዲያሪዮ ጎል ነው።

የላ ሊጋው ታላቅ ክለብ የሜዳን ላይ ቁጥጥሩን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስፈልገው ቢያውቅም ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚቀርበው ዋጋ ግን መነሻው 100 ሚ.ዩሮ እንደሚሆንም ያውቃል።


አርሰናል ደሚራቤን ለማስፈረም እየተፋለመ ነው


አርሰናል የሆፈኒየሙን አማካኝ ከሬም ዴሚራቢን ለማስፈረም ከኤቨርተን ጋር ለመፋለም መዘጋጀቱን የኒውስ ሞንዶ ዘገባ አመልክቷል።

መድፈኞቹ ለጀርመናዊው ተጫዋች መደባኛ የሆነ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ የተዘጋጁ ቢሆንም፣ ከፕሪሚየር ሊጉ ተቀናቃኛቸው ኤቨርተን ግን ከባድ ፉክክር የሚጠብቃቸው ይሆናል። 


ማን ዩናይትድ በጊራማልዶ ዝውውር ተረቷል


ማንችስተር ዩናይትድ የቤኔፊካውን ተከላካይ ግሪማልዶን ለማስፈረም የሚያደርገውን ፉክክር በሴሪ ኣው መሪ ናፖሊ መረታቱን ኦ ጆጎ ዘግቧል።

የጣሊያኑ ክለብ ለስፔናዊው ተጫዋች 30 ሚ.ዩሮ ለመክፈል በመስማማት ሆዜ ሞሪንሆ የግራ ተከላካይ ለማዛወር የሚያደረጉትን ጥረት ወደሌላ ተጫዋች እንዲያዞሩ አስገድዷቸዋል።


ማን ዩናይትድ ጉሃላምን የማዛወር ዕድሉ ከፍ ብሏል


ናፖሊ አሌኻንድሮ ግሪማሎን ለማስፈረም በመቃረቡ የግራ ክንፍ ተጫዋቹ ፉኣዚ ጉሃላምን ለማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ተዘጋጅቷል። ዘገባው የሪከርድ ነው።

አልጄሪያዊው ተጫዋች ለሴሪ አው ክለብ አዲስ ኮንትራት ያፈረመው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ በቦታው ሁነኛ ምትክ እየመጣበት የሚገኝ በመሆኑ ናፓሊዎች 53 ሚ.ፓ በሆነ የውል ማፍረሻ ዋጋው ለዩናይትድ ለመሸጥ ፈቃደኛ ናቸው። 


ክሎፕ ናይክ በኮቲንሆ ዝውውር ጉዳይ “አፈትልኮ” ባወጣው መረጃ ተበሳጭተዋል


የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ “ቸል ሊባል የማይችል” ሲሉ ናይክ ፊሊፔ ኮቲንሆ ለባርሴሎና እንደሚሸጥ አፈትልኮ የለቀቀውን መረጃ ኮንነዋል።

የቀዮቹ አሰልጣኝ በርንሌይን 2ለ1 ከረቱ በኋላ ለጋዜጠኞቹ በሰጡት መግለጫ ያነበቡት የናይክ መረጃ ምንም እንዳልሆነ በመግለፅ ብራዚላዊው የጨዋታ አቀጣጣይ አሁንም የእቅዳቸው አካል እንደሆነ ገልፀዋል።


ዊሊያን በቼልሲ እንደሚቆይ ዳግመኛ ተናግሯል


የቼልሲው የክንፍ ተጫዋች ዊሊያን ከብራዚሉ ኢኤስፒኤን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በክለቡ ለመቆየት ቁርጠኛ መሆኑን ዳግም ገልፅዋል።

ብራዚላዊው ተጫዋች በማንችስተር ዩናይትድ ከሆዜ ሞሪንሆ ጋር ዳግም እንደሚቀላቀል ስሙ በከፍተኛ ተያይዞ ቢቆይም፣ ተጫዋቹ ግን ስታምፎርድ ብሪጅን የመልቀቅ ሃሳብ እንደሌለው ገልፅዋል።


ሞሪንሆ አዲስ ተጫዋች የማከል ውጥን አላቸው


ሆዜ ሞሪንሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወቅት አዲስ ፊት ወደማንችስተር ዩናይትድ ቡድን እንደሚቀላቅሉ ለእንግሊዙ የስፖርት ቴሌቭዥን ስካይ ስፖርትስ ተናግረዋል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ በርካታ ከሆኑ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ብቃት ካላቸው ተጫዋቾ ጋር ስማቸው የተያያዘ ሲሆን፣ ክለባቸው ያለማሸነፍ ጉዞውን ለመግታት ሲሉም አዳዳስ ተጫዋቾችን የማዛወር ፍለጎት አላቸው።


ዊልሼር ከአርሰናል ጋር አዲስ ስምምነት እንደሚያደረግ ፍንጭ ሰጥቷል


የአርሰናሉ አማካኝ ጃክ ዊልሼር በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በግል የኢንስታግራም ገፁ ላይ በለጠፈው መልዕክት ከክለቡ ጋር አዲስ የስራ ዘመን እንዲኖረው ቁርጠኛ መሆኑን ገልፅዋል።

እንግሊዛዊው ተጫዋች በኤመራትስ ስታዲየም ከኮንትራት ነፃ ለመሆነ ከተቃረቡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ቢሆንም፣ ከክለቡ ጋር ያለውን ቆይታ ለመቀጠል ዕቅድ እንዳለው ጠቁሟል።


ባርሳ የኡምቲቲ ፈላጊዎችን ሊከላከለ ነው


ባርሴሎና የማንችስተር ከተማ ክለቦቹ በሳሙኤል ኡምቲቲ ላይ ያለቸውን ፍላጎት ለመከላከል ሲል ከፈረንሳያዊው ተከላከዩ ጋር አዲስ ኮንትራት ስለሚፈረረምበት ጉዳይ ለመነጋገር ዕቅድ መያዙን የስፔኑ ጋዜጣ ማርካ ዘገባ አመልክቷል።


አርሰናል ሉካስን ዳግመኛ ወደክለቡ ለመጥራት አቅዷል


አርሰናል ለዲፖርቲቮ ላ ከሩኛ በውሰት የሰጠውን አጥቂውን ሉካስ ፔሬዝን ዳግመኛ የመጥራት አማራጭ ዕቅድ መወጠኑን ዘ ሚረር ጋዜጣ ዘግቧል።

ስፔናዊው አጥቂ በአርሰናል ቆይታው ተቸግሮ በማሳለፉ ባለፈው ክረምት በውሰት ወደሃገሩ ተመልሶ ነበር። ነገር ግን አሁን አርሰን ቬንገር የአጥቂ አማራጫቸውን ከፍ የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ ሉካስን ወደክለቡ ሊመልሱት ይችላሉ።

Advertisements