አርሰናል ከ ቼልሲ | የለንደን ደርቢ ጨዋታ ቅድመ ቅኝት

አርሰናል እስከአራት ባለው ደረጃ ውስጥ ገብቶ የውድድር ዘመን ጉዞውን ለማስቀጠል የለንደን ተቀናቃኙን በኤመራትስ ያስተናግዳል። መድፈኞቹ በጥር ወር ውስሥት በሜዳቸው ከማንችስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል ጋር ያደረጓቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ በጣሏቸው ነጥቦች በአሁኑ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከቶተንሃም በሁለት ነጥቦች ዝቅ ብለው በስድሰኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም የአርሰን ቬንገሩ ቡድን የውድድር ዘመናቸውን ለመታደግ የበላይ ስድስት ደረጃ ውስጥ ከሚገኙት ተቀናቃኞቻቸው መካከል አንዱ ከሆነው ቼልሲ በዚህ ጨዋታ ውጤት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

እንግዳዎቹ ቼልሲዎች ደግሞ በደረጃ ሰንጠረዡ ከሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው የ2018 ጉዟቸውን ከፍ ባለ የጋለ ስሜት ውስጥ ሆነው ተያይዘውታል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአዲስ ዓመት በዓል ወቅት በቀላሉ ኤቨርተንን መርታቱን ተከትሎ ሰማያዊዎቹ ቀደም ባሉት ቀናት ይዘውት የነበረውን የሁለተኛ ደረጃ መልሰው በማግኘትና ሲቲዎች የውጤት መንሸራተቶች እንዲገጥሟቸው በመመኘት ከዚህ ጨዋታ ሶስት ነጥቦችን የማግኘት እቅድ ይዘው የሚጫወቱም ይሆናል።

ውድድር፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ቀን፡ ረቡዕ ታህሳስ 25፣ 2010 ዓ.ም
ሰዓት፡ ምሽት 4፡45
ሜዳ፡ ኤመራትስ ስታዲየም
የጨዋታው ዳኞች፡ 

ይህን ጨዋታ በመኃል ዳኛነት የሚመሩት የ39 ዓመቱ አንቶኒ ቴለር ናቸው
  • ዋና ዳኛ፡ አንቶኒ ቴለር
  • የመስመር ዳኞች፡ አዳም ኑን፣ ሊ ቤትስ
  • አራተኛ ዳኛ፡ ክሬግ ፓውሰን 

የሁለቱ ክለቦች የከዚህ ቀደም አይረሴ ጨዋታ

ሰማያዊዎቹ ለመረጨሻ ጊዜ ወደኤመራትስ ባቀኑበት መስከረም 2016 የደረሰባቸውን የ3ለ0 ሽንፈት ፈፅሞ ሊያስታውሱት የሚፈልጉት ጨዋታ አይደለም። ይሁን እንጂ አንቶኒዮ ኮንቴ ከዚያ ጨዋታ በኋላ ከ4-2-3-1 አጨዋወት በውድድር ዘመኑ ለዋንጫ ድል ወዳበቃቸው እና በጁቬንቱስ የአስልጣኝነት ዘመናቸው ስኬታማ ወደሆኑበት ወሳኙ የ3-4-3 ለውጥ እንዲሸጋገሩ ምክኒያት የሆናቸው ጨዋታ ነበር። ከዚያ ጨዋታ በኋላም ሰማያዊዎቹ ከኋላ ሶስት ተከላካዮችን በመጠቀም በተከታታይ 13 ጨዋታዎችን ድል ማድረግ ችለዋል።

መደፈኞቹ በዚያ ጨዋታ በአሌክሲ ሳንቼዝ፣ ቲዮ ዋልኮት፣ እና መሱት ኦዚል ግቦች የበላይነታቸውን ያረጋገጡበትን ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

የክለቦቹ ወቅታዊ ውጤት

ቼልሲ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ከገባበት የውጤት መንገራገጭ በማገገም ለመጨረሻ ጊዜ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች አስሩን በድል አጠናቋል። ከዚህም ሽንፈት የገጠመው በአንዱ ጨዋታ ብቻ ነው። ሰማያዊዎቹ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያላቸው በሁለተኛ ደረጃ ከሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች በሁለት ነጥብ ዝቅ ብለው ይገኛሉ።

አርሰናል ባለፉት ሳምንታት ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አራቱን በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ፍሬ አልባ ጉዞን እያደረገ ይገኛል። ይህ ደግሞ የአርሰን ቬንገሩን ቡድን በአሁኑ ጊዜ በአራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሊቨርፑል በአራት ነጥቦች ዝቅ ብሎ በስድስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አስገድዶታል።

የቡድኖቹ ወቅታዊ ዜና

አርሰናል

አርሰን ቬንገር በሃውትሮንሱ ጨዋታ ጉዳት የገጠማቸውን ላውረን ኮሸልኒ እና ሲአድ ኮላሲናችን ጨምሮ ከዋናው ቡድን ከስድስት የማያንሱ ተጫዋቾችን በቡድናቸው ውስጥ ሳያካትቱ ይህን ጨዋታ ሊያደረጉ ይችላሉ። ሁለቱም ተከላካዮች ከጨዋታው በፊት በሚደረግላቸው የአቋም መለኪያም በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ያለመሰለፋቸው ነገር የሚረጋገጥ ይሆናል።

ሳንቲ ካዛሮላ፣ ኦሊሺየ ዥሩ እና ናቾ ሞንሪል በገጠማቸው የረዥም ጊዜ ጉዳት አሁንም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ሲሆን፣ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመቱ ዋዜማ ከምዕራብ ለንደኑ ቡድን ጋር ወደዌስት ብሮም ካቀናው ቡድን ጋር አብሮ ያልተጓዘው መሱት ኦዚል በዚህ ጨዋታ በጥቂቱም ቢሆን መሰለፍ ዕድል እንደሚኖረው ቬንገር ተናግረዋል።

ቼልሲ

ኤዲን ሃዛርድና ሴስክ ፋብሪጋስ ስቶክን 5ለ0 በረታው ቡድን ውስጥ ተሰለፈው ያልነበረ ሲሆን፣ በዛሬው ምሽት ጨዋታ ግን ወደተሰላፊነቱ እንደሚመለሱ ይጠበቃል። አንድሪያስ ክርስቲያንስን በገጠመው ህመም ከብራይተን ጋር በተደረገው የቦክሲንግ ደዩ ጨዋታ ያልተሰለፈ ሲሆን፣ ከፓተርሶቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይም ግልጋሎት ያልሰጠ ተቀያሪ ተጫዋች ነበር። በመሆኑም ዴንማርካዊው ተጫዋች ከለንደን ተቀናቃኞቻቸው ጋር በሚያደረጉት በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ ተሰላፊ ሆኖ ሊጫወት ይችላል። ከዚህ ውጪ አንቶኒዮ ኮንቴ ከደርቢው ጨዋታ በፊት ምንም ዓይነት አብይ የሚባል የአዲስ ጉዳት ዜና የለባቸውም።

ግምታዊ አሰላለፍ

የአርሰናል ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች: ቼክ፣ ቻምበርስ፣ ሙስታፊ፣ ኮሸልኒ፣ ቤለሪን፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ኮላሲናች፣ ዌልቤክ፣ ላካዜቲ፣ ሳንቼዝ 

የቼልሲ ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች: ኮርትዋ፣ አዝፒሊኩዌታ፣ ክርስቲያንሰን፣ ሩዲገር፣ ሞሰስ፣ ካንቴ፣ ፋብሪጋዝ፣ አሎንሶ፣ ዊሊያን፣ ሞራታ፣ ሃዛርድ 

የእርስ በርስ ግንኙነታቸው ቁጥራዊ መረጃዎች

  • አርሰናል ሁለቱ ክለቦች ባለፈው የውድድር ዘመን በዚሁ ሜዳ ባደረጉት ተመሳሳዩ ጨዋታ ከዚያ ቀደም ከቼልሲዎች ጋር በአምስት ጨዋታዎች ላይ የነበራቸውን ያለማሸነፍ ጉዞ (አቻ3 ሽንፈት2) 3ለ0 በሆነ ውጤት በመርታት መግታት ችለዋል።
  • በሁሉም ውድድሮች ላይ እንደቼልሲ ኤመራት ስታዲየም በመምጣት አርሰናል ድል ማድረግ የቻለ ክለብ የለም። በዚህም (5 ጨዋታ) የሚስተካከለው ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ነው።
  • አርሰናል በሁለቱም የፕሪሚየር ሊግ የደረሶ መልስ ጨዋታዎች ከ2011-12 (ድል1 አቻ1) ወዲህ በቼልሲ ሳይሸነፍ ያጠናቀቀበት የውድድር ዘመን የለም ። በሁለቱም የውድድር ዘመን የደረሶ መልስ ጨዋታ ግቡን ሳያስደፍር ያጠናቀቀው ደግሞ በ1998-99 ነበር።
  • አርሰናል ከቼልሲ ጋር በፕሪሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ በሰባቱ ላይ ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል። በእነዚህ ጨዋታዎች ላይም ኳስና መረብን ማገናኘት የቻለው አራት ጊዜ ብቻ ነው።
  • ቼልሲ በዚህ የውድድር ዘመን ካስቆጠራቸው ግቦች 21 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው በስፔናውያን ተጫዋቾቹ አማካኝነት ነው። ይህ ደግሞ ከየትኛውም የአውሮፓ አበይት አምስት ሊግ ክለቦች የሚልቅ ነው።
  • ይህ ጨዋታ ካለፈው የውድድር ዘመን መጀመሪያ አንስቶ በሁሉም ውድድሮች በአርሰን ቬንገር እና በአንቶኒዮ ኮንቴ መካከል የሚደረግ ስድስተኛ ጨዋታ ሲሆን፣ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ደግሞ የቼልሲው አሰልጣኝ አንድ ጨዋታ ብቻ ድል ሲያደርጉ በሁለት ጨዋታ ሽንፈት ገጥሟቸው ሁለቱን ዳግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።
  • ሴስክ ፋብሪጋዝ በአርሰናል ተጫዋችነት ዘመኑ በኤመራትስ 19 ግቦችን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ በተቃራኒ ሆኖ በተጫወተባቸው (በሶስት ጨዋታ ለቼልሲ ተሰልፎ) ጨዋታዎች ግን እስካሁን በመድፈኞቹ ላይ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።
Advertisements