የቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች የነበረው ጂያንፍራንኮ ዞላ አልቫሮ ሞራታን መከረ

1.jpg

ቼልሲዎች ወደ ኤምሬትስ ስታድየም አቅንተው 2-2 በተለያዩበት የእሮብ ምሽቱ ጨዋታ ላይ ስፔናዊው አልቫሮ ሞራታ ሊታመን በማይችል መልኩ ተደጋጋሚ ግልጽ የጎል እድሎችን መጠቀም ባለመቻሉ ትችቶች እየቀረቡበት ይገኛሉ፡፡ የቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች የነበው ጂያንፍራንኮ ዞላም ተጫዋቹ ውጤታማ ለመሆን ምን ማድረግ እንደሚገባው ምክሩን ሰጥቶታል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የለንደን ደርቢ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል በሄክቶር ቤለሪን በጭማሪ ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ከቼልሲ ጋር ሳይሸናነፍ 2-2 በሆነ ውጤት መለያየት ችሏል፡፡

በሁለተኛው ግማሽ 4 ጎሎች በታየበት ጨዋታ ቼልሲዎች አሸናፊ ለመሆን እጅግ ተቃርበው የነበሩ ቢሆኑም እስከመጨረሻ የታገሉት አርሰናሎች ከሽንፈት የዳኑበትን ጎል በቤለሪን አማካኝነት ማግኘት ችለዋል፡፡

በሁለቱም ቡድኖች መካከል ጥሩ ጥሩ የጎል እድሎች ተፈጥረው የነበሩ ቢሆኑም እንደ ስፔናዊው ሞራታ ግን በተደጋጋሚ ግልጽ የግብ አጋጣሚ ያገኘ አልነበረም፡፡ሞራታ ሶስት ግልጽ የግብ እድሎች ተፈጥረውለት ከፒተር ቼክ ፊትለፊት ተገናኝቶ አንዱንም መጠቀም አለመቻሉ አስገራሚ ሆኗል፡፡

ተጫዋቹም ለቼልሲዎች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ምክንያት የሆነ ሲሆን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችቶችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

3.jpg

የቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች የነበረው ጣሊያናዊው ጂያንፍራንኮ ዞላም በሞራታ መበሳጨቱን በመናገር ለወደፊት በእንግሊዝ ውጤታማ ለመሆን ምን ማድረግ እንደሚገባው ምክሩን ለግሶታል፡፡“የሳታቸውን ኳሶች ለማመን ይከብዳል ምክንያቱም የሜዳ ላይ ትጋቱ ጥሩ ነበር፡፡ትናንትም ቢሆን ለቡድኑ የሚተጋ ተጫዋች መሆኑን አሳይቷል፡፡ነገርግን እውነቱን ለመናገር ትንሽ ተበሳጭቼ ነበር፡፡

“በኔ እምንት ሞራታ ምርጥ ተጫዋች የሚሆን ነው፡፡ነገርግን እንደ ትናንቱ አይነት በተለይ በመጀመሪያው ግማሽ ያልተጠቀመበት ኳስ ስትመለከት ቀዝቀዝ ትላለህ፡፡ስለዚህ አይምሬ መሆን ይጠበቅበታል፡፡እሱ አስደናቂ ብቃት ያለው ተጫዋች ነው፡፡ነገርግን ወደ ቼልሲ ሲመጣ ትንሽ ያጠራጠረኝ ነገር ቢኖር ጠንካራ እና የማይምር ሆኖ መቀጠሉን ነበር፡፡ሲል አስተያቱን ሰጥቷል፡፡”

ሞራታ ዲያጎ ኮስታን ለለቀቀው ቼልሲ የረጅም ጊዜ ተተኪ ሆኖ ወደ ለንደን መምጣቱ ይታወሳል፡፡

 

 

Advertisements