የተጠናቀቀ / አርሰናል በዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

የጥር የዝውውር መስኮት መከፈቱን ተከትሎ አርሰናል የመጀመሪያ ፈራሚውን በይፋ አስተዋወቀ።

አርሰናል ግሪካዊው የ 20 አመቱ ወጣት ተጫዋች ኮንስታንቲኖስ ማቭሮፓኖስ ከ ፓአስ ጂያኒና ማስፈረማቸውን አሳውቀዋል።

ማቭሮፓኖስ መድፈኞቹ የክለባቸው አዲሱ መልማይ የሆነው ስቨን ሚስሊንታት ከቀጠሩ በኋላ ያስፈረሙት የመጀመሪያ ተጫዋች ሆነዋል።

ተጫዋቹ ለግሪክ ከ 21 አመት በታች የሚጫወት ሲሆን ቦታውም በመሀል ተከላካይነት እንደሆነ ታውቋል።

በአጨዋወቱም ጥሩ አቅም ያለው መሆኑን ለክለቡ ማሳየት በመቻሉ ለአርሰናሎች ለወደፊት ጥሩ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

 በተለይ በአየር ላይ አጨዋወቱ እና በሰውነት ንክክ ላይ ባመዘነ አጨዋወት ብቁ መሆኑ ለፕሪምየርሊጉ ምቹ ተጫዋች እንደሆነ ታውቋል።

ተጫዋቹን ለማዘዋወር አርሰናል 1.9 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ እንዳደረገ የታወቀ ሲሆን በቂ የመጫወት እድል እንዲያገኝ በውሰት ወደ ሌላ ክለብ እንደሚያመራ ይጠበቃል።

Advertisements