የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማቱን ማን ያሸንፍ ይሆን?

ከፈረንሳዩ ጋዜጣ ፍራንስ ፉትቦል አዘጋጅነቱን እ.ኤ.አ. በ1992 ተረክቦ ጅማሮውን ያደረገው የካፍ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓት ሀሙስ ታህሳስ 26 በጋና ዋና ከተማ አክራ ይካሄዳል።

በዘንድሮው ሽልማት በአውሮፓ ትልልቅ ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱት ሀለቱ የሊቨርፑል ከዋክብት ግብፃዊው መሐመድ ሳላህና ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ እንዲሁም የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ጋቦናዊ አጥቂ ፒየር ኤምሪክ አውባምያንግ ለሽልማቱ ታጭተዋል። 

የ25 ዓመቱ መሐመድ ሳላህ ባለፈው የውድድር ዘመን ዓመት በጣሊያኑ ክለብ ሮማ ያስቆጠራቸውን 31 ግቦችን ጨምሮ በክረምቱ የዝውውር ወቅት በ39 ሚ.ፓ የእንግሊዙን ሊቨርፑል ከተቀላቀለ በኋላ በአስደናቂ ሁኔታ ከወዲሁ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ካስቆጠራቸው 17 ግቦች ጋር በሁሉም ውድድሮች ለይ ለቀዮቹ 21 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። እንዲሁም ሃገሩን ግብፅን ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ የዓለም ዋንጫን እንድትቀላቀል ማድረግ ችሏል።

የ27 ዓመቱ አውባምያንግ ባለፈው የውድድር ዘመን በጀርመኑ ቡንደስሊጋ 31 ኳሶችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ተጫዋቹ የዘንድሮውን ሽልማት አሸናፊ የሚሆን ከሆነ ይህን ሽልማት የሚያገኝ የመጀመሪያው ጋቦናዊ ተጫዋችም ይሆናል።

ለዚህ ሽልማት የታጨው አፍሪካዊ ተጫዋች ሌላው የሊቨርፑል ተጫዋች ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ነው። የ25 ዓመቱ ማኔ ባለፈው የውድድር ዘመን በየርገን ክሎፑ ቡድን ሊቨርፑል ድንቅ የሚባል ጊዜን ከማሳለፉም ባሻገር ሃገሩ ሴኔጋልን ለዓለም ዋንጫ ተሳትፎ እንድተበቃ ቀላል የማይባል አስተዋፅኦ ማድረግ ችሏል።

ስለአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ሊያወቋቸው የሚገቡ እውነታዎች

  • አይቮሪኮስታዊው የማንስተር ሲቲው አማካኝ ያያ ቱሬ ከ2011 አንስቶ በተከታታይ ለአራት ጊዜያት ያህል ይህን ሽልማት የማሸነፍ ክብረውሰኑን ይዟል።
  • ካሜሮን ለአራት ጊዜያት ያህል ሽልማቱን ያሸነፈውን ሳሙኤል ኤቶን ጨምሮ 11 ሽልማት ብዙ ጊዜ ሽልማቱን በማሸነፍ ስኬታማ ሃገር ናት።
  • የቀድሞው የቼልሲ እና የጋና ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ ማይክል ኢሴን እ.ኤ.አ. ከ2005 አንስቶ በተከታታይ ለሶስት ጊዜያት ያህል ቢታጭም በአንዱም ላይ ግን ሽልማቱን ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።
  • ግብጠባቂዎቹ ካሜሮናዊው ቶማስ ን’ኮሎ (ሁለት ጊዜ) እና ሞሮኳዊው ባዱ ዛኪ ይህን ሽልማት ማግኘት የቻሉ ሲሆን ይህን ሽልማት ያገኘ አንድም ተከላካይ ግን የለም። ከአማካኝ ተጫዋቾች ዳግሞ ሌላው ሞሮኳዊ መሐመድ ቲሞሚ ሽልማቱን ማግኘት ችሏል።
  • ይህን ሽልማት ለአራት ጊዜያት ያህል ማሸነፍ የቻሉትን ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኢቶ እና ያያ ቱሬን ጨምሮ እንደምዕራብ አፍሪካውያኑ ሃገራት ጠራርጎ የወሰደ አፍሪካዊ ቀጠና የለም።
Advertisements