የዕለተ ሀሙስ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

አዲስ በተከፈተውና ከተጀመረ አራት ቀናትን ባስቆጠረው የአውሮፓ የጥር የዝውውር መስኮት ክለቦች በየፊናቸው የተጫዋች ስብስባቸው ለማጠናከር ይፋዊና ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ደፋ ቀና እያሉ ይገኛል። ይህን እንቅስቃሴያቸውን ደግሞ የስፓርቱ መገናኛ ብዙኃን ከስር ከስር እየተከታተሉ በመዘገብ ላይ ይገኛሉ። ኢትዮአዲስ ስፖርትም የአበይት መገናኛ ብዙኃኑን ውሃ የሚያነሱ አጫጭር የዝውውር ዘገባዎችን መራርጣ ወደናንተ እነሆ ትላለች።

ቼልሲ ለሮናልዶ ዝውውር የዝውውር ዋጋ ሊያቀርብ ነው


ቼልሲ ለሪያል ማድሪዱ ልዕለኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዝውውር ዋጋ ከሚያቀርቡ ሶስት ክለቦች መካለል አንዱ እንደሆነ የስፔኑ ጋዜጣ ዶን ባሎን ዘገባ አመልክቷል።

ፓርቱጋላዊው ተጫዋች ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማርን ለማስፈረም በሚያደረገው ጥረት ደስተኛ ባለመሆኑ ሳንቲያጎ በርናባውን የመልቀቅ ዕቅድ ይዟል። 

የቀድሞው የዩናይትድ ተጫዋቹ ወደእንግሊዝ ሊመለስ የሚችልበት ዕድል ቢኖርም፣ ነገር ግን ቼልሲ ከፒኤስጂ እና ከአሜሪካኑ ክለብ ኤልኤ ጋላክሲ ቀላል ፉክክር አይጠብቀውም።


ፒኤጂ ኮንቴን እየማተረ ነው


የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ አንቶኒዮ ኮንቴን የኡናይ ኤምሬ ምትክ ለማድረግ እያጤነበት የሚገኝ መሆኑን የጣሊያኑ ጂፓንሉካ ዲ ማርዚዮ ዘገባ አመልክቷል።

የሊግ 1 መሪው ስፔናዊውን አሰልጣኝ በክረምቱ የሚያሠናብት ሲሆን፣ በምትካቸውም ባለፈው የውድድር ዘመን ቼልሲን ለፕሪሚሊጉ ዋንጫ ያበቁትን ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ የሚቀጥር ይሆንል።

ኮንቴ በአሁኑ ጊዜ በስታንፎርድ ብሪጅ መረጋጋት የላቸውም።

አርሰናል የማቭሮፓኖስን ዝውውር አጠናቀቀ

አርሰናል የግሪኩ ክለብ፣ ፓስ ጂፓኒና ክለን ተጫዋች የሆነውን ኮንሳንቲኖስ ማቭሮፓኖስን ዝውውር አጠናቋል።

የእንግሊዝ ጋዞጦች ሌሎች አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

daily mail

 • ማንችስተር ዩናይትድ ጆዜ ሞሪንሆ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ዳግም ለክለቡ የመፈረም አለመፈረማቸው ነገር አለመረጋገጡ አስግቶታል።
 • የስቶክ ሲቲው አሰልጣኝ ማርክ ሂዩዝ በመጥፎ የውጤት ጉዞ ውስጥ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ስለወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ከክለቡ ቦርድ ጋር ሊነጋገሩ ነው።
 • ቶተንሃሞች የሃሪ ኬን ደመወዝ በሳምንት 200 ሺህ ፓውንድ በማድረግ የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛው ተከፋይ እንግሊዛዊ ተጫዋች ሊያደርጉት ተዘጋጅተዋል።
 • ሲቪያ የኤቨርተኑን አጥቂ ሳንድሮ ራሚሬዝን የማስፈረም ፍላጎት አለው።

daily star

 • ዋትፎርዶች የሰንደርላንዱን አማካኝ ዲዲየ ንዶንግን፣ የሌስተሩን አጥቂ ኢስላም ስሊማኒን እና የሊቨርፑሉን ላዛር ማርኮቪችን በጥር ወር የማስፈረም ፍላጎት አለው።
 • ሳውዛምፕተን፣ ዌስት ሃም፣ ኒውካሰል እና ኤቨርተን በአርሰናል የማይፈለገውን የክንፍ ተጫዋች፣ ቲዮ ዋልኮትን ለማስፈረም እየተፎካከሩ ነው።
 • የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ሄናሪክ ሚክሂታሪያን ወደኢንተር ለመዛወር የሚያደረገውን እንቅስቃሴ አግደዋል።
 • አጥቂው ካምሮን ጀሮም ኖርዊችን ለመልቀቅ ነፃ ሲሆን፣ በ1 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋም በቀድሞ ሁለት ክለቦቹ፣ ካርዲፍና በርሚንግሃምም የሚፈለግ ተጫዋች ሆኗል።
 • የፖርትስማውዙ አሰልጣኝ ኬኒ ጃኬት የመሰመር ተከላካዩን ሲልቪያን ቤስላንድስን እና አማካኙን ኮነር ሮናንን በውሰት ለማስፈረም ወደቀድሞ ክለባቸው ዎልቭስ ዳግም ተመልሰዋል።

daily mirror

 • ሊቨርፑል የፊሊፔ ኮቲንሆ ምትክ ይሆነው ዘንድ 90 ሚ.ፓ. ዋጋ ባለው የሞናኮው ተጫዋች ቶማስ ለማር ላይ ትኩረቱን አድርጓል። 
 • ኤቨርተን ከቤሽኪታሹ ፕሬዝዳንት ጋር የፊት ለፊት ንግግር ካደረጉ በኋላ ሴኒል ቱሰንን ለማስፈረም ተቃርበዋል።
 • ሮቢ ኪን ፕሪሚየር ሊጉን ለመቀላቀል የተቃረቡት ዎልቭሶችን በመቀለቀል በአስገራሚ ሁኔታ ዳግም በፕሪሚየር ሊጉ ሊጫወት ይችላል።
 • ዌስት ብሮሞች ጆን ኢቫንስ ለክለቡ አዲስ ኮንትራት የመፈረም ቁርጠኝነት የማይኖረው ከሆነ ሊሸጡት የተዘጋጁ ሲሆን፣ ማንችስተር ዩናይትድና ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ፈላጊዎቹ ናቸው።
 • ኸደርስፊልዶች የኖርዊቹን አማካኝ አሌክስ ፕሪቻርድን ለማስፈረም ሶስተኛ የዝውውር ዋጋ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።
 • ኢንተር ሚላኖች የማንችስተር ዩናይትዱን ኹዋን ማታን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።

daily express

 • የስዊድኑ ክለብ ኦስቴርሰንደስ የተዘነጋውን የሴልቲክ አማካኝ ሊያም ጀደርሰንን የማስፈረም ፍላጎት አለው።

the sun

 • ጆዜ ሞሪንሆ በ50 ሚ.ፓ እንዲፈረም የክለቡ ቦርድ መወትወታቸውን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን የመስመር ተከላካይ ዳኒ ሮዝን በዝውውር ዒላማቸው ውስጥ አስገብተውታል።
 • ሰርጂዮ አጉዌሮ የማንችስተር ሲቲ የረጅም ጊዜ የወደፊት ቆይታውን አስመልክቶ በጨለማ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግሯል።

the independent

 • ጁቬንቱስ አሌክስ ሳንድሮን በዚህ ወር በክለቡ እንዲቆይ የማድረግ ቁርጠኝነቱን በማሳየቱ ፈላጊዎቹን ማንችስተር ዩናይትድና ቼልሲን ተስፋ አሳጥቷል።
Advertisements