የነፖግባን የዳብ ዳንስ በሜዳ ላይ ያሳየው የሳኡዲው ተጫዋች የእስር ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል

ሳኡዲ አረቢያዊው ተጫዋች በዓለም አቀፉ የስፓርት ደጋፊው ዘንድ ዝነኛ የሆነውን የደስታ መግለጫ እንቅስቃሴ በማሳየቱ ራሱን ከባድ ችግር ውስጥ ከቷል። 

እንደቢቢሲ ዜና ዘገባ ከሆነ ለሳኡዲው አል ኖጁም ክለብ የሚጫወት አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ተጫዋች በክለቡ የረቡዕ ዕለት ጨዋታ በተቀያሪ ወንበር አከባቢ ዝነኛውን የዳብ ዳንስ እንቅስቃስቃሴ ሲያደርግ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች ተለቀዋል።

የዳብ ዳንስ ደግሞ በሳኡዲ አረቢያ እንደዕፅ ተጠቃሚዎች ማሳያ ተደርጎ የሚወስድ በመሆኑ የተከለከለ እንቅስቃሴ ነው።

ቢቢሲ የዜና ተቋም ከዚህ ቀደም እንደዘገበው ከሆነም አብደላክ አል ሻሃኒ የተሰኘ አርቲስት በነሃሴ ወር ላይ በተካሄድ የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ይህንኑ የዳብ እንቅስቃሴ በማሳየቱ ለእስር ተዳርጓል።

እግርኳስ ተጫዋቹም የተከለከለውን አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረጉና ህግን በመተላለፉ ቅጣቱ ተግባራዊ ይደረግበት አይደረግበት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ዳብ በበርካታ ዝናኛ የስፖርቱ ዓለም ተጫዋቾች የደስታ መግለጫ በመሆን የሚታወቅ (እጆችዎን ለማንቀሳቀስ በቂ ጊዜ ከሌለዎት) ደናሹ ጭንቅላቱን ወደመሬት ዘምበል አድርጎ በአንደኛው እጁ ላይ በማሳረፍ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ለሌኛውን እጁን ወደላይ ከፍ አደርጎ የሚወዛወዝበት የሂፕ-ሆፕ ዳንስ ነው።

Advertisements