የዕለተ ሰኞ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የተከፈተው የአውሮፓ የጥር ወር የዝውውር መስኮት አዳዲስ የዝውውር ዜናዎችን ማሰማቱን ቀጥሏል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም ዛሬ በአበይት ሚዲያዎች የተዘገቡ አጫጭር የዝውውር ወሬዎችን እንደሚከተለው አንደሚከተለው አሰናድታለች።

ቼልሲ ሎፍተስ ቺክን አይሸጥም

ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ እንደዘገበው ከሆነ ክሪስታል ፓላስ በክለቡ በውሰት ላይ የሚገኘውን አማካኙን ሩበን ሎፍተስ-ችክን በቋሚነት የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ቢገልፅም፣ ባለቤት ክለቡ ቼልሲ ግን ተጫዋቹን የመሸጥ ዕቅድ የለውም።

አርዳ ቱራን ወደቱርክ ለመዛውር ተቃርቧል

የባርሴሎናው አማካኝ አርዳ ቱራን ወደእናት ሃገሩ የቱርኩ ክለብ ባሳክሴሂር ለማምረት መቃረቡን የቱርኩ ሳብህ ዘገባ አመልክቷል።

ኒውካሰል ዩናይትድ ኬኔዲን እንደሚያስፈርም ተስፋ አድርጓል

ኒውካሰል ዩናይትድ በስዋንሲ በውሰት ቆይታ ላይ የሚገኘውን ኬኔዲን ዝውውር እንደሚየጠናቅቅ ተስፋ ማድረጉን ኢቭኒንግ ሳታንዳርድ ዘግቧል።

ቬንገር ሊወጡ አርቴታ ደግሞ አርሰናልን በዋና አሰልጣኝነት ሊይዝ ነው 

አርሰን ቬንገር ከክለቡ ጋር ያለቸውን የአንድ ዓመት ከግማሽ ኮንትራት ከወዲሁ ገተው የሁለት አስርት ዓመታት የክለቡ ቆይታቸውን ለመቋጨት መዘጋጀታቸውን ደይሊ ሚረር ዘግቧል።

ፔፕ፣ ሲቲ ከቫንዳይክም በላይ ለአሌክሲስ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርቧል

ፔፕ ጋርዲዮላ ክለቡ ማንችስተር ሲቲ ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል ያስፈረመውን የሳውዛምፕተኑን ተከላካይ ቪርጅል ቫን ዳይክን ከሚያስፈርምበት ማንኛውም ሁኔታ በላይ ለአርስናሉ ኮከብ አሌክሲ ሳንቼዝ ቅድሚያ እንዲሰጥ መጠየቁን የሜትሮ ዘገባ አመልክቷል፡

ኮቲንሆ ለዝውውሩ መሳካት በግሉ ክፍያ ፈፅሟል

እንደዘታይምስ ዘገባ ከሆነ ፊሊፔ ኮቲንሆ በ142 ሚ.ፓ. ከሊቨርፑል ወደባርሰሎና የሚያደረግውን ዝውውር ለማሳካት ሲል የተወሰነ ክፍያ ከራሱ ኪሱ ለመክፈል ስምምነት ፈፅሟል።

“ስፐርስ ኬንን በክለቡ እንዲቆይ ሊያስገድድው አይችልም”

አሰልጣኙ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የሪያል ማድሪድ የዝውውር ዒላማ የሆነው ሃሪ ኬን የመልቀቅ ምኞት ካለው ቶተንሃም ሊሸጠው እንደሚገደድ ማመናቸውን የጎል ድረገፅ ዘገባ አመልክቷል።

ሪያል ማድሪድ የኮርቱዋና ሃዛርድ ፈላጊ ሆኗል

ሁለቱ የቼልሲ ተጫዋቾች ኤዲን ሃዛርድ እና ቲብዋ ኮርትዋ የሪያል ማድሪድ የክረምቱ ዝውውር ቀዳሚ ዒላማ መሆናቸውን የዘገበው ስካይ ስፖርትስ ነው።

የፒኤስጂው ሞራ ወደዩናይትድ የመዛወር ከፍተኛ ፍላጎት አለው

የፒኤስጂው ተጫዋች ሉካስ ሞራ ወደማንችስተር ዩናይትድ መዛወርን የጥር ወር ቀዳሚ ምርጫው ማድረጉን የደይሊ ስታር ዘገባ አመልክቷል።

ማን ዩናይትድ እና ቼልሲ በፖርቶው ማሬጋ ዝውውር ፉክክር ይዘዋል

ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ የፖርቶው አጥቂ ሞሳ ማሬጋ የሚሸጥ ተጫዋች ስለመሆኑ አለመሆኑ ለክለቡ ጥያቄ ማቅረባቸውን ሜትሮ ዘግቧል።

ባርሳ ሚናን አስፈረመ

ባርሴሎና ኮሎምቢያዊውን የመሃል ተከላካይ የሪ ሜናን ከፓልሜራስ ክለብ ለማዛወር ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ ማጠናቀቁን የስፔኑ አስ ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል።

ሊቨርፑል ኪያታ ወደክለቡ የሚመጣበትን ጊዜ እያፋጠነ ነው

ሊቨርፑል ፊሊፔ ኮቲንሆን ለባርሴሎና ከሸጠ በኋላ ናቢ ኪየታን ከአርቢ ሌፕዚግ የሚያመጣበት ጊዜ እንደሚፋጠን ተስፋ ማድረጉን ዘ ቴሌግረፍ ዘግቧል። 

መሲ ኮቲንሆ በዴምቤሌ ቦታ እንዲጫወት ይፈልጋል

የባርሴሎናው ኮከብ ሊዮኔል መሲ ፊሊፔ ኮቲንሆ በክለቡ የመጀመሪያ ተሰላፊነት ቦታን ከዴምቤሌ እንዲያገኝ መፈለጉን የስፔኑ ዲያሪዬ ጎል ዘገባ አመልክቷል።

Advertisements