ዩዚያን ቦልት በቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሙከራ ዕድል አገኘ

​የአለማችን ፈጣኑ ሰው ዩዚያን ቦልት በጀርመኑ ታላቅ ክለብ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ መጫወት የሚያስችለውን የሙከራ ዕድል ማግኘቱ ተሰማ፡፡

የ100 እና 200 ሜትር የአለም ክብረወሰን ባለቤቱ ቦልት በተደጋጋሚ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች የመሆን እንዳለው ሲናገር የሚደመጥ ሲሆን ለማንችስተር ዩናይትድ የመጫወት ፍላጎቱንም ደብቆ አያውቅም፡፡የ31 አመቱ ጃማይካዊ ከሰንደይ ኤክስፕረስ ጋር በነበረው ቆይታ “በመጪው መጋቢት ወር በቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሙከራ ዕድልን አግኝቻለሁ ፤ ፕሮፌሽናል ተጫዋች የመሆን ዕቅዴ በዛ የሙከራ ወቅት ይወሰናል፡፡” ብሏል፡፡
ቦልት አክሎም “ትችላለህ ካሉኝ ተጨማሪ ልምምድ ማድረግ ያስፈልገኛል ፤ አደርገዋለው፡፡ ስሜታዊ ያረገኛል ፡፡ በቀላሉ ስሜታዊ የምሆን ሰው ባልሆንም ይህ የተለየ ነው፡፡ለመረጋጋት  የተወሰነ ጊዜ የስፈልገኛል ጥቂት ጨዋታዎችን ካደረኩ በኋላ ነገሮችን ማስኬድ አይቸግረኝም” ብሏል፡፡

የቦልት ስፖንሰር የሆነው ፑማ የዶርትሙንድ የትጥቅ ስፖንሰር ሲሆን ይህንን የሙከራ ጊዜ በማመቻቸቱ ረገድም ተሳታፊ እንደነበረው ታውቋል፡፡

ስለማንችስተር ፍላጎቱ የተጠየቀው ዩዚያን “ከቀድሞው የዩናይትድ አለቃ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር የመነጋገሩን ዕድል አግኝቼ ነበር ፤ ጥሩ ተስፋን ሰጥቶኛል፡፡ ዝግጁነቴን ካረጋገጠ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ነግሮኛል ” በማለት ቦልት የኤክስፕረስ ቆይታውን አጠቃሏል፡፡

Advertisements