ቺሊ ኮሎምቢያዊውን አሰልጣኝ ቀጠረች

ቺሊ የቀድሞውን የኮሎምቢያ አሰልጣኝ ሪየናልዶ ሩዳን እስከ 2022 የዓለም ዋንጫ ድረስ አዲስ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጋ መቅጠሯን በይፋ ገልፃለች።

ሩዳ ቺሊን ለሩሲያው ዓለም ዋንጫ ማብቃት ያልቻሉትን ተሰናባቹን ኹዋን አንቶኒዮ ፒዚን ተክተው ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት የሚመሩም ይሆናል። 

የ60 ዓመቱ አሰልጣኝ እስከ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ መጨረሻ ድረስ ቡድኑን ለመምራት የተስማሙ ሲሆን፣ ቺሊ በውድድሩ ላይ ጥሩ ደረጃ የምትበቃ ከሆነም ኮንታራታቸውን ከዚያም በላይ ማደስ የሚችሉ ይሆናል።

ሩዳ ኮሎምቢያን (ከ2004-06) እና ሆንዱራስን (2007-10) በአሰልጣኝነት መርተዋል።

ከቺሊ በፊት ለመጨረሻ ጊዜም ፍላሚንጎ ክለብን በማሰልጠን ላይ ነበሩ።

Advertisements