በፍሊፔ ኮቲንሆ ዝውውር ላይ የተቀመጡት ተጨማሪ ክፍያዎች(Add-ons)ምን ምን ያካትታሉ?


ብራዚላዊው ፍሊፔ ኮቲንሆን ለማዘዋወር የካታላኑ ቡድን 142 ሚሊየን ፓውንድ እንዳወጣ ቢነገርም ከዚህ ውስጥ 36 ሚሊየን ፓውንዱ[Add-ons] ግን ለወደፊት በተለያዩ ሁኔታዎች የሚከፈሉ ናቸው።እነዚህ ክፍያዎች ምን ምን ያካትታሉ?

ኮቲንሆ በተከፈተው የጥር የዝውውር መስኮት ከቀናት በፊት ወደ ባርሴሎና ማቅናቱ ይታወሳል።ባሳለፍነው ሰኞም የህክምና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ በይፋ ከደጋፊዎች ጋር በካም ኑ ተዋውቋል።

ተጫዋቹን ለማዘዋወር ባርሴሎና ከባለፈው የክረምቱ የዝውውር መስኮት ጀምሮ ያደረገው ጥረት በመጨረሻም ማሳካት ችሏል።

የመጀመሪያ ጨዋታውንም ከጉዳቱ ሲያገግም ከ 20 ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ይጠበቃል።

ባርሴሎና ለተጫዋቹ ዝውውር በአጠቃላይ 142 ሚሊየን ፓውንድ እንዳወጣ ቢነገርም ከተጠቀሰው ሂሳብ ውስጥ 36 ሚሊየን ፓውንዱ ለወደፊት በተለያየ መንገድ በተጨማሪ[Add-ons] የሚከፈሉ ናቸው።

ይህ ማለት ደግሞ ባርሴሎና ለሊቨርፑል በጥሬ ገንዘብ የከፈለው 106 ሚሊየን ፓውንድ ሲሆን ከውሉ ጋር ለወደፊት በተለያዩ ሁኔታዎች ተጨማሪ[Add-ons] 36 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፈል ይሆናል።

ከ 36 ሚሊየን ፓውንድ ውስጥ ግማሹ [18 ሚሊየን ፓውንድ] ኮቲንሆ 100 ጨዋታዎችን ለባርሴሎና መጫወት ከቻለ የሚከፈል ነው።

አከፋፈሉም ተጫዋቹ በየ 25 ጨዋታዎች ባርሴሎና 4.5 ሚሊየን ፓውንድ ለሊቨርፑል ይከፍላል።[4.5*4 = 18 ሚ]

ቀሪው 18 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፈለው ደግሞ ባርሴሎና በቻምፒየንስ ሊግ ከሚኖረው ተሳትፎ እና ውጤታማነት ጋር የተያያዙ ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 4.5 ሚሊየን ፓውንድ ቡድኑ በ 2018/2019 በቻምፒየንስ ሊግ ላይ መሳተፍ ከቻለ እንዲሁም በተጨማሪ 4.5 ሚሊየን ፓውንድ ደግሞ በ 2019/2020 ላይ በድጋሚ መሳተፍ ከቻለ የሚከፈል ይሆናል።

ከላይ የተጠቀሱት የውድድር አመቶች ማለትም በ 2018/2019 በቻምፒየንስ ሊግ ላይ ባርሴሎና ዋንጫ ካነሳ 4.5 ሚሊየን ፓውንድ እንዲሁም በ 2019/2020 በተመሳሳይ በቻምፒየንስ ሊጉ ዋንጫ ካነሳ ሌላ 4.5 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍል ይሆናል።

Advertisements